እስራኤል የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ የረጅም ጊዜ ቃል አቀባይ የነበረውን አቡ ኦቤይዳን መግደሏን ገለጸች

የእስራኤል ጦር የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ የረጅም ጊዜ ቃል አቀባይ የነበሩትን ሰው መግደሏን አስታወቀች፡፡ አቡ ኦቤይዳ የተባለው ይህ ሰው በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት መገደሉን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሩ ለቃል አቀባዩ ግድያ የእስራኤል መከላከያን እና የእስራኤልን የደህንነት ኤጀንሲን አመስግነዋል፡፡

አክለውም እንከን የለሽ አፈጻጸም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ሃማስ ግድያውን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡ የእስራኤል ጦር ግን በፈጸመው የአየር ጥቃት ቃል አቀባዩ ተገድለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ ቀደም ብለው የቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ የረጅም ጊዜ ቃል አቀባዩ አቡ ኦቤይዳ የእስራኤል ኢላማ መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡ ኔትንያሁ አቡ አሁን አብሮን እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ከካቢኒያቸው ጋር በነበራቸው የስብሰባ ወቅት ለሚኒስትሮቻቸው ገልጸዋል፡፡ በሃማስ በኩል ግን ይህን የሚያጠራ ሰው እስካሁን አልተሰማም፡፡

ከዚያ በኋላ ግን እስራኤል ካትዝ አቡ መገደሉን ይፋ አድርገዋል፡፡ አቡ አርብ እለት እስራኤል በጋዛ ያሰበችው አዲሱን ዘመቻ የመጀመሪያ ምዕራፍ እንደጀመረችው የሚገልጽ ይዘት ያለው መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡

አርብ እለት የእስራኤል ጦር በጋዛ ሲቲ ዘመቻ ጀምሯል፡፡ ከቅዳሜ ጀምሮ ከ40 በላይ ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል የተባለ ሲሆን፤አብዛኞቹ በጋዛ ከተማ ነው የተገደሉት፡፡

ቃል አቀባዩ አቡ አርብ እለት ስለ እስራኤል አዲሱ የጋዛ ዘመቻ በተመለከተ መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡ የቡድኑ የረጅም ጊዜ ቃል አቀባይ የሆነው አቡ ኦቤይዳ ሃማስ ከቀሩት ጥቂት ወታደራዊ ክንፍ አመራሮች መካከል አንዱ ነበረ፡፡//

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe