እስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

የኢፌዴሪ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የእስራኤል ፕሬዝዳንት ክቡር አይዛክ ሄርዞግን በማለዳው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተቀብለው አስጎብኝተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በመላው ጥቁር ሕዝቦች ዘንድ የነፃነት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደውን የዓድዋ ድል ታሪክ፣ ለሀገር ሉዓላዊነት ሕይወታቸውን የገበሩ ጀግኖችን ዝክረ-ታሪክ እና በሙዚየሙ የሚገኙ ቅርሶችን ተመልክተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር የከፈሉትን ዋጋ የሚዘክረውን ሙዚየም በዝርዝር ተመልክተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንቱ ለታሪካዊው ስፍራ የሰጡትን ትኩረት በማድነቅ፣ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ ያላቸው ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።

ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ እና ባህላዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ክቡር ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለነበራቸው ጊዜ እያመሰገንን፤ በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሳችን እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ እንመኛለን።” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe