የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ዋጋን እስከ 500 ፐርሰንት የሚያስወድደው መመርያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑ ተሰማ።
ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን የወጣው የሶስተኛ ወገን የሀላፊነት ገደብን ተከትሎ የፕሪሚየም ዋጋ እስከ 500 ፐርሰንት መጨመሩ ተመላላክቷል።
በተሻሻለው የሶስተኛ ወገን የሀላፊነት መመርያ መሰረት ለአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት ቀደም ሲል ተፈፃሚ የነበረው 2 ሺህ ብር ወደ 15 ሺህ ብር እንዲያድግ ተደርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሚደርስ የሞት አደጋ እስከ 40 ሺህ ብር የነበረው ክፍያ አሁን እስከ 250 ሺህ ብር እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ለአካል ጉዳት እስከ 40 ሺህ ብር ክፍያ ይፈጸም የነበረው በአዲሱ ውሳኔ 250 ሺህ ብር ድረስ እንዲሆን ተደርጓል።

