እናት ባንክ ለራይድ አሽከርካሪዎች የመኪና መግዢያ ብድር እንደሚሰጥ አስታወቀ

ከእናት ባንክ ጋር አብረው ለሚሰሩ የራይድ አሽከርካሪዎች የመኪና ግዢ ብድር እንደሚሰጥ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሚያስ አንዳርጌ ገልፀዋል። በእናት ባንክ በኩል የመኪና ግዢ ብድር ያገኙ የራይድ አሽከርካሪዎች የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ፡፡
እናት ባንክ ከሃይብሪድ ዲዛይንስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ራይድ (RIDE) ጋር በመተባበር ለመስራት የሚያስችል የስራ መግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመ ጊዜ ጀምሮ ባንካችን የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመስጠትና የብድር አማራጮችን በማቅረብ ከራይድ አሽከርካሪዎች ጎን መሆኑን አሳይቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል የራይድ አገልግሎት ክፍያ (Ride commission/ Service charge) እንዲሁም ግብራቸውን በወቅቱ ለመክፈል፣ አደጋ ሲገጥማቸው ጥገና ለማከናወን እና ተያያዥ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያግዛቸውን የብድር አማራጮችን አቅርበናል፡፡ በዚህም የብድር አገልግሎት በሺዎች የሚቆጠሩ የራይድ አሽከርካሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
እናት ባንክ ከሃይብሪድ ዲዛይንስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ራይድ (RIDE) ጋር በመተባበር ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ባዘጋጀው የምሳ ፕሮግራም ላይ የመኪና ግዢ ብድር ያገኙ የራይድ አሽከርካሪዎች፣ የሃይብሪድ ዲዛይንስ ኃ/የተ/የግል ማህበር (ራይድ) እና የእናት ባንክ የስራ አመራር በተገኙበት ብድሩን ላገኙ አሽከርካሪዎችን መልካም የስራ ዘመን በመመኘት ወደስራ እንዲገቡ አድርጓል::
በእነዚህ እና ወደፊትም በምናቀርባቸው የራይድ አሽከርካሪዎችን ያማከሉ ልዩ የብድር አማራጮች እንዲሁም ባንኩ በሚያቀርባቸው የተለያዩ ማበረታቻዎች ተጠቃሚ ለመሆን ዛሬ ነገ ሳይሉ አሁኑኑ የእናት ባንክ ደንበኛ መሆን ደንበኝነቶን በማጠናክረው ይቀጥሉ ሲል  ባንኩ አስታውቋል ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe