እናት ባንክ ለ60 እናቶች የበዓል ስጦታ አበረከተ

እናት ባንክ ከእንደዜጋ ማህበራዊ እንደራሴ አገር በቀል ድርጅት ጋር በጋራ በመተባበር ከዚህ ቀደም የ’እናት ለእናትን‘ ስልጠና ለወሰዱ 60 እናቶች ‘’ስላንቺ እንደዜጋ እናመስግን‘’ በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የ’እናት ለእናት‘ ቤተሰባዊ የበዓል ስጦታ በዛሬው እለት በባንኩ ዋና መስሪያቤት አበርክቷል፡፡
ባንኩ ከእንደዜጋ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና ፅዳት ላይ ለተሰማሩ እናቶች ስልጠናዎችን በመስጠትና በማደራጀት፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲያግዙ የማድረግ አላማን የሰነቀ ‘’እናት ለእናት‘’ የተሰኘ ፕሮጀክት ነድፎ በሶስት ወር ሰርቶ ማሳያ ፕሮጄክቱ ተተግብሯል፡፡

እናት
የስጦታው ዋና ዓላማ በጎዳና ፅዳት ላይ ለተሰማሩና ‘’በእናት ለእናት‘’ ፕሮጄክት ተሳታፊ ለነበሩ እናቶች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከማገዝ ጋር በተያያዘ የበዓል ስጦታ በመስጠት የባንኩን ቤተሰብነት ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ ነው፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ እናት ባንክ በዛሬው ዕለት ለተለያዩ የማህበረሰባችን ክፍሎች ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያደርጉ ለአራት የተመረጡ የበጎ አድራጎት ተቋማት ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የነበረውን ቁርጠኛ የማህበራዊ ኃላፊነት የመወጣት የድጋፍ ተግባራት ለመከወንና የእንኳን አደረሳችሁ የበዓል ስጦታ ታሳቢ በማድረግ የፋይናንስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በተጨማሪም ከላይ ከተገለጹት ከዚህ ቀደም የ’እናት ለእናትን‘ ስልጠና ከወሰዱ 60 እናቶች ጋር በተያያዘ እናት ባንክ፣ እንደዜጋ ማህበራዊ እንደራሴ እና አነጋ ኢንጂነሪንግ የእናቶቹን የገቢ አቅማቸውን ማሳደግ መሠረት ያደረገና በዘላቂነት በኢኮኖሚ ለማብቃት ዓላማን በማድረግ በሶስትዮሽ በጋራ ተባብሮ ለመስራት የክፍለ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች በተገኙበት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
እናት ባንክ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ፍላጎት በሚያሟላ፣ የሴቶችን የፋይናንስ አካታችነት በሚያጎለብት አሠራርና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን ጨምሮ የተለያዩ ምቹና በርካታ አገልግሎቶችን በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት እናት ባንክ በተቀማጭ ሒሳብ፣ በብድር በሰጠው የገንዘብ መጠንና፣ በተከፈለ ካፒታል ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ጠንካራና ውጤታማ ባንክ ነው፡፡ እንዲሁም ባንኩ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ከ161 በላይ የአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎችን በመክፈት ለሁሉም ማኅበረሰብ ተደራሽ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት የባንኩ አጠቃላይ አፈጻጸም እጅጉኑ ውጤታም ሲሆን፣ በሒሳብ ዓመቱ ከሌሎች ባንኮች በተለየ የትርፍ ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ በቀዳሚነት መጠቀስ ችሏል፡፡
SourceDire tube

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe