እናት ፖርቲ ብልፅግናንና ኢዜማን የሚፎካከር ፖርቲ ሆነ

የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቅን አስመልክቶ በዛሬው እለት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መገለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ፦- ሁሉም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ወይም በፈጠሩት ትብብር/ህብረት አማካኝነት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች 49 ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ውስደዋል።

– ምርጫ ምልከት ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች ውስጥ 47 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል።

– 47ቱ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 8209 እጩዎች አስመዝግበዋል።

– ከፍተኛ እጩ ካስመዘገቡ ፓርቲዎች መካከል የመጀመሪያው ብልፅግና ፓርቲ ሲሆን 2,432 እጩዎች አስመዝግቧል ፣ 2ተኛ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1,385 እጩዎች አስመዝግቧል ፣ 3ተኛ ደግሞ እናት ፓርቲ ሲሆን 573 እጩዎች አስመዝግቧል።

– የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እጩዎቻቸውን ያላስመዘገቡ ፓርቲዎች ናቸው።

– በአጠቃላይ እጩ ካስመዘገቡት 47 ፓርቲዎች ውስጥ 4 ለክልል 2 ደግሞ ለፓርላማ የሚወዳደሩ ናቸው።

– 125 እጩ ተወዳዳሪዎች በግል ተመዝግበዋል።

– በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ችግሮች አጋጥመው ነበር ፤ ከ16 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታዎችን አቅርበው መፍትሄ ተሰጥቷቸዋል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe