ከመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ

በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ከአካላዊው የጦር ግንባር አልፎ ወደ ዲጂታሉ ዓለም ተሸጋግሯል። የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች እንደሚጠቁሙት፣ ግጭቱን ተከትሎ በመንግሥታዊ ተቋማት እና በወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘሩ የአጸፋዊ የሳይበር ጥቃቶች (Retaliatory Cyberattacks) በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረው ታይተዋል። ይህም አሁናዊ ጦርነቶች ከወታደራዊ ግንባር ባሻገር በዲጂታሉ ዓለምም ከፍተኛ ጥቃት የሚፈጸምባቸው እንደሆነ ትልቅ ማሳ ነው፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ በ16 ሀገራት ውስጥ በሚገኙ 110 ተቋማት ላይ 149 የሚደርሱ የአገልግሎት ንፍገት (Distributed Denial of Service – DDoS) ጥቃቶች መድረሳቸውን የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች ገልጸዋል:: ይህ ጥቃት በ16 ሀገራት ላይ የተሰራጨ ሲሆን፣ በጂኦ-ፖለቲካዊ የሳይበር ጦርነት ውስጥ የታየ ከፍተኛ የጥቃት ለውጥ መሆኑ ተመላክቷል።
ጥቃቱ በዋናነት የመንግሥት መሠረተ ልማቶችን ኢላማ በማድረጉ የመንግሥት ተቋማት ከጠቅላላው ጥቃት 47.8%፣ የፋይናንስ ተቋማት 11.9% እንዲሁም የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ 6.7% መሆኑን ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል፡፡
ራድዌር በሪፖርቱ ላይ እንደገለጸው የዲጂታል ግንባሩ ከአካላዊው ጦርነት ጎን ለጎን እየሰፋ መሄዱንና አጥቂዎቹ ዘዴያቸውን ከቀላል የድረ-ገጽ ማበላሸት ወደ ውስብስብ እና የመንግሥት መሠረተ ልማቶችን ወደ ማሽመድመድ እንዳሳደጉት ገልጿል። ይህም የሳይበር ጥቃት ሚስጥራዊ የመንግሥት መረጃዎችን በማውጣት የጂኦ-ፖለቲካ አጀንዳዎችን ለማስፈጸም እየዋለ እንዳለ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
በአጠቃላይ በመካከለኛው ምስራቅ የታየው የሳይበር ጥቃት መበራከት የዲጂታል ደህንነት ከሀገራዊ ደህንነት ጋር ምን ያህል እንደተሳሰረ ትልቅ ማሳያ ነው። ጥቃቶቹ በዋናነት የመንግሥት፣ የፋይናንስ እና የቴሌኮም ዘርፎችን ኢላማ ማድረጋቸው፣ ተቋማት የአገልግሎት ንፍገት የሳይበር ጥቃት መከላከያ ስልቶችን እና የመረጃ ጥበቃ ስርዓታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ማጠናከር እንዳለባቸው ያስገነዝባል። ከአካላዊ ግጭት ጎን ለጎን የሚካሄደው ይህ የዲጂታል ጦርነት ለወደፊትም መሰል የጂኦ-ፖለቲካ ውጥረቶች ሲፈጠሩ ሀገራት ምን ዓይነት የሳይበር ስጋቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ የሚማርቡት ትልቅ ክስተት ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe