ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል አማራጭ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

ከሚያዚያ 16 2015  ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል አማራጭ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ከቴሌ ብር በተጨማሪ ሌሎችም የክፍያ ሥርዓቶችን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ክፍያ በ ” ቴሌ ብር ” ብቻ እንደሚፈፀም እያሳወቀ ይገኛል።

ባለፉት ተከታታይ ቀናትም ቢሮው የመኪና ባለቤቶች በቀሩት ጥቂት ቀናት የነዳጅ ክፍያ በ” ቴሌ ብር ብቻ ” እንደሚከፈል በመገንዘብ ከእንግልት ለመዳን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ እያሳወቀ ነው።

ቢሮው መሰል መልዕክቶችን በተረጋገጠ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎቹ ነው ለህዝብ እያሰራጨ የሚገኘው።

ለመሆኑን የነዳጅ ክፍያ ከ ” ቴሌ ብር ” ውጭ መፈፀም አይቻልም ?

ኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ” #ነዳጅ ” የተባለ የሞባይል መተግበሪያ ማቅረባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

መተግበሪያው ተገልጋዮች የነዳጅ ክፍያቸውን ከንግድ ባንክ አካውንታቸው የተርጋ ቁጥራቸውን ብቻ በመጠቀም መክፈል ያስችላል ያለ ሲሆን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የነዳጅ ክፍያው ” በቴሌ ብር ብቻ ” ነው የሚፈፀመው እያለ ለህዝብ እያሰራጨ ያለው መልዕክት ትክክል እንዳልሆነ አስረድቷል።

” ነዳጅ ” የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ ከክፍያ አማራጭነት በተጨማሪ አሽከርካሪዎች አቅራቢያቸው የሚገኙትን ማደያዎች ከአቅርቦታቸው ጋር ማግኘት የሚችሉበት አማራጭም እንዳለው ድርጅቱ ገልጾልናል።

የክፍያ አማራጩ በሀገሪቱ ከሚገኙ ማደያዎች 60 በመቶ ማዳረስ መቻሉንም ጠቁሟል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe