ከቀናት በፊት አልሞትኩም ብለው ሬሳ ሳጥን ያንኳኩት ኢኳዶሯዊት ‘የእውነት’ ሞቱ

ባለፈው ሳምንት ሊቀበሩ ሲሉ ሬሳ ሳጥን አንኳኩተው ሞትን ለጥቂት ያመለጡት የ76 ዓመቷ አዛውንት በድጋሚ ሬሳ ሳጥን ውስጥ ገብተዋል።

ሐዘንተኞችን ባስደነገጠ ሁኔታ አልሞትኩም ብለው ከሬሳ ሳጥን የወጡት እኚህ ሴት አሁን ሬሳ ሳጥን ውስጥ የተከተቱት መሞታቸው በሐኪም በማያሻማ ሁኔታ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

በኢኳዶር ባባሆዮ በምትባል ከተማ ነዋሪ የሆኑትና እማማ ቤላ ሞንቶያ በሚል ስም የሚታወቁት እኒህ ሴት ከሬሳ ሳጥን ከወጡ በኋላ መኖር የቻሉት ለጥቂት ቀናት ብቻ ነው።

በለቀስተኞች መሀል ‘ሞትን እምቢኝ ብለው የተነሱት የእማማ ቤላ ሞንቶያ ከተከተቱበት የሬሳ ሳጥን አንኳኩተው መውጣታቸው ታላቅ ዜና ሆኖ የነበረው ባለፈው ሳምነት ነበር። ከሬሳ ሳጥኑ ከወጡ በኋላ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል የቆዩት ሴት ከሰባት ቀናት በኋላ በጨረፍታ ወደተመለከቱት ሞት ጠቅልለው ተመልሰዋል።

በዚህ ወቅት ሞታቸው በሐኪሞች ብቻ ሳይሆን በኢኳዶር ጤና ሚኒስቴር ጭምር ነው የተረጋገጠው። የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴርም አሁን ሞታቸው ‘የእውነት’ ነው ብሏል። የሟች ልጅ ጊልበርት ባርበራም ቢሆን ለአገሬው ጋዜጣ “አሁን እናቴ መሞቷ እርግጥ ነው፤ ከዚህ ኋላ ሕይወቴ እንደ ቀድሞው በፍጹም አይሆንም” ሲል በሐዘን ተናግሯል።

እማማ ቤላ ሞንቶያ በሚል ስም የሚታወቁት ሟች በፈረንጆቹ ሰኔ 16 ቀን ከሬሳ ሳጥን ከወጡ በኋላ በተደረገላቸው ምርመራ ያጋጠማቸው ነገር ምንድን ነበር የሚል ምርመራ ተደርጎ ነበር። ሐኪሞች ‘ካታለፕሲ’ የሚሉት እክል እንደሆነ ነው የደረሱበት። ‘ካታሌፕሲ’ ሰዎች ራሳቸውን የሚስቱበትና ሰውነታቸው የሚደርቅበት የጤና እክል ነው።

SourceBBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe