ከተማ አስተዳደሩ የሸገር ዳቦን ከአርብ ጀምሮ አንድ ዳቦ በአምስት ብር ማቅረብ እንደሚጀምር አስታወቀ

በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረው ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት ከፊታችን ከአርብ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ጀምሮ ዳግም መከፋፈል እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡
በቢሮው የንግድ እና ግብይት ዘርፍ ም/ ቢሮ ኃላፊ መስፍን አሰፋ፤ የሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት አርብ ዳግም እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት የአንድ ዳቦ ዋጋ 5፡00 ብር መሆኑን የገለጹት ም/ቢሮ ኃላፊው፤ በአቅርቦት ረገድም በኹሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዳቦ በላይ የሚያመርተው ድርጅቱ በተለይ ከስንዴ አቅርቦትና ግዢ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ክፍተት ምርቱ በመዲናዋ ማሰራጭት ካቆመ ከስድስት ወራት በላይ ማስቆጠሩ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe