ከንብረት ጋር በተገናኘ ፍች የፈጸሙ ባለትዳሮችን ሲያዋዛግብ የቆየ ነው የተባለው ህግ ላይ ትርጉም ተሰጥቶበታል ተባለ፡፡
ከትዳር በፊት በተፈራ የግል ንብረት ላይ አዲስ የህግ ትረጉም መሰጠቱ የብዙ ባለትዳሮችን ጥያቄ መልሷል እተባለ ነው፡፡ የፌደሬሽን ም/ቤት የህገ-መንግስት አጣሪ ጉባኤ እስካሁን ፍርድቤቶች ስራ ላይ ሲያውሉት የቆየውን ህግ ትርጉም እንዲሰጠው በማድረግ ቀይሮታል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሠረት ባል ወይም ሚስት ከጋብቻ በፊት ባፈሩት ቤት ላይ ከጋብቻ በኋላ ወጭ በማውጣት ማሻሻያ ወይም ማስፋፊያ ካደረጉበት ቤቱ የጋራ ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ አሁን የተደረገው የህግ ትርጉም ይህንን ሙሉ በሙሉ ለውጦታል፡፡
የፌደሬሽን ም/ቤት ይህ ለረጅም ጊዜ ፍርድ ቤቶች ሲገለገሉበት የቆው አሰራር አግባብ አይደለም ቤቱን ለማሻሻል የወጣው ወጭ ተጣርቶ ለአንደኛው ወገን እንዲሰጠው ያደርገዋል እንጂ ቤቱን የጋራ አያደርገውም የሚል የህግ ትርጉም ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሰጥቷል፡፡
የፌደሬሽን ም/ቤት ውሳኔ የብዙዎችን ጥያቄ የመለሰ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ የፌደሬሽን ም/ቤት የህግ ትርጉም የሰጠው ከህገ መንግስቱ የንብረት የማፍራት መብት ጋር ይቃረናል በሚል ነው፡፡

