ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ በአገር አቀፍ ደረጃ የለዉጡን ሂደት ከገመገምገ በሗላ በበጎ ጎኑ ተመልክቷታል። ይሁን እንጅ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ፤ፀጥታ እና ብሄራዊ አንድነትን ከማስጠበቅ አኳያ ለዉጡ የመቀለበስ አደጋ እንደተጋረጠበት አዴሃን ያምናል። የለዉጥ ሃይል ነኝ የሚሉ የመንግስት አካላት ሳይቀር የእኔ የእኔ ብቻ በሚል አመለካከት አብሮነትን አደጋ ዉስጥ በሚጥል ተግባር ተዘፍቀዋል።
የሁላችንም ኢትዮጵዊያን ዋና ከተማ የሆነችዉን አዲስ አበባን የብቻየ ከተማ ነች ብሎ መንቀሳቀስ ፍፁም ተቀባይነት የለለዉ ተግባር መሆኑን አዴሃን ያምናል።
እንዲሁም በአለፉት ዓመታት በመሬት ወረራ ተጠምዶ የቆየዉ ህወሃት /ወያኔ በሃይል የያዛቸዉን የወልቃይት የራያ የመተከል የአማራ ቦታዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስት እንዲመልስ እየጠየቅነ ጉዳዮን ለማድበስበስ እና ቀጥተኛ ያልሆነ መልስ ለመስጠት የሚደረጉ ሙከራዎችን አጥብቀን እንቃወማለን።መንግስት በቅርቡ በአቋቋመዉ የወሰን እና የማንነት ኮሚሽን አማካኝነትም ሆነ በፈለገዉ ተቋም ጥያቄዉን ቢመልስ ተቃዉሞ የለንም። ይሁን እንጅ ጥያቄዉ ሳይመለስ ቀርቶ በእነኚህ አካባቢዎች ለሚደርስ ማንኛዉም አይነት ጉዳት መንግስት ሃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን አዴሃን ማስገንዘብ ይወዳል።
በደካማዉ ኢህአዴግ መንግስት አቅም ማነስ በህወሓት /ወያኔ እብሪት እና ማን አለብኝነት ምክንያት በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በዜጎች ላይ በደረሰባቸዉ የሰባዊ እና ቁሳዊ ዉድመት የተሳተፍ የመንግስት አካለት እና ግጭት በመቀስቀስ የጦር መሳሪያ በማቀበል እገዛ ያደረጉ የህወሓት /ወያኔ አመራሮች እና ወታደራዊ መኮንንኖች ለህግ እንዲቀርቡ አዴሃን በአፅንኦት ይጠይቃል።
አዴፓ የራሱን የዉስጥ ሽኩቻ እና ችግር ለመሸፈን ያመቸዉ ዘንድ ከሕግ ውጭ የወሰደብንን ንብረት እንዲመልስ እና አዴሃንን ለማፍረስ ከሚያደርገዉ እንቅስቃሴ እንዲቆጠብ እንናሳስባለን።
መንግስት ከኤርትራ ለተመለሱ ታጋዮች የመልሶ ማቋቋሙን በአስቸኳይ እንዲጀምር እንጠይቃለን።
የአማራ ትግል ያሸንፋል!
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe