ከአርቲስት ማህሙድ አህመድ የምስጋና ዝግጅት የተገኘው አጠቃላይ 118 ሺህ ዶላር ገቢ ለማህሙድ ተበረከተ

ከአርቲስት ማህሙድ አህመድ የምስጋና ዝግጅት የተገኘው አጠቃላይ አንድ መቶ አስራ ስምንት ሺህ ዶላር ገቢ ለጋሽ ማህሙድ ተበረከተ።
ለአንጋፋው አርቲስት ማህሙድ አህመድ በቨርጂኒያ፣ ስፕሪንግፊልድ በተካሄደው የምስጋና ምሽት የተገኘው ገቢ ዛሬ የዝግጅቱ ስፖንሰሮች፣ አርቲስቶች፣ አጋር ድርጅቶችና ግለሰቦች በተገኙበት ለጋሽ ማህሙድ ተበርክቷል። በዚህም መሰረት በምስጋና ምሽቱ ከቲኬት ሽያጭና ከዝግጅት ስፖንሰሮች የገኘው $105,300 (አንድ መቶ አምስት ሺህ ሶስት መቶ የአሜሪካን ዶላር) አርቲስቱ ገቢ ተደርጓል። ጋሽ ማህሙድ ሳይቸግረው፣ የተረጋጋና የሰከነ ህይወትን ይመራ ዘንድ ይሄው ከአሜሪካ የተሰበሰበው ገንዘብ የተቀመጠለት ልክ እንደ ጡረታ ክፍያ በየወሩ እየወሰደ እንዲጠቀምበት በሚያስችል የትረስት ፈንድ አካውንት ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የዝግጅቱ ብቸኛ የሚድያ አጋር የሆነው ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ዝግጅቱን ቀርጾ ለማስተላለፍ እና ከማስታወቅያ የተገኘውን ብር 1,623,525 (አንድ ሚሊየን፣ ስድስት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ አምስት የኢትዮጵያ ብር) ለጋሽ ማህሙድ ገቢ ተደርጓል። ባጠቃላይ የተገኘው ገቢ በአሁኑ ምንዛሬ ወደ 15.5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር ነው።
ለዚህ አላማ መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ስፖሰሮችና ተባባሪ ድርጅቶችና ግለሰቦችም የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል። ጋሽ ማህሙድም ለተደረገለት ሁሉ የዝግጅቱን አስተባባሪወችና በዝግጅቱ ላይ የተሳተፉትን ሁሉ አመስግኗል። የዝግጅቱ አስተባባሪወችም ጋሽ ማህሙድን አክብረን ለመከበር በተሰናዳው በዚህ ታላቅ ዝግጅት ላይ የየበኩላችሁን ላበረከታችሁ፣ በዝግጅቱ ለታደማችሁ፣ በሃሳብ ለደገፋችሁ ሁሉ በአርቲስት ማህሙድ አህመድ ስም ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።
ሞና ጓደኞቹ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe