ከአዲስ አበባ ወደ አዋሽ መልካሳ የተላኩ የወለጋ ተፈናቃዮች በቂ ሠብዓዊ ድጋፍ አላገኘንም አሉ

ከወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ አካባቢ ተጠልለው የነበሩ ከ100 በላይ ሰዎች ወደ አዋሽ መልካሳ ከተማ ተገደው ቢወሰዱም፣ በቂ ሠብዓዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው አለመሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን በየጊዜው በሚፈጠረው የፀጥታ ችግር ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ አካባቢ ተጠልለው የነበሩ ሰዎች ለአዲስ ማለዳ እንደገለፁት፣ የካቲት 17/2014 በከተማ አስተዳድሩ ውሳኔ መሠረት በፀጥታ አካላት ታጅበው አርሲ ዞን አሰላ ከተማ መርሲ ወረዳ ገብተው የነበረ ሲሆን፣ የሚያስተናግዳቸው የመንግሥት አካል አለማግኘታቸውን ተከትሎ ወደ ምስራቅ ሸዋ ዞን አዋሽ መልካሳ (አዋሽ ጎርጎ) ከተማ እንዲመለሱ ቢገደዱም፣ በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው እና የመጠለያ ችግር እንደገጠማቸው ተናገረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe