ከኢትዮጵያ ህዝብ 7 ሚሊዮን  የሚሆነዉ ሲጋራ አጫሽ መሆኑ ተነገረ

ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ቁጥር ውስጥ አምስት በመቶ የሚሆነው ትንባሆ እንደሚያጨስ የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ይህ ቁጥር ከሌሎች ሀገራት ቁጥር አንፃር አነስተኛ ቢመስልም በኢትዮጵያ ካለው የህዝብ ቁጥር ሰባ በመቶ የሚሆነው ወጣት በመሆኑ ለትንባሆ  በቀላሉ ሊጋለጥ እንደሚችል የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
እንደ ሄራ ገርባ ማብራሪያ በህገወጥ መንገድ የሚገቡት የተለያየ ፍሌቨር ያለዉ ትንባሆ መቆጣጠር ካልተቻለ ጣዕሙ የተለየ በመሆኑ ጀማሪ አጫሾች በቀላሉ ሊያማልሉ እና ሊጋብዝ እንደሚችል ስጋታቸዉን አስቀምጠዋል፡፡ በዓለም አቀፋ ደረጃ ትንባሆ የተከለከለ ሳይሆን ቁጥጥር ሊደረግበት የሚችል በመሆኑ ኢትዮጵያ ቁጥጥሯን አጠናክራ ከቀጠለች ለውጥ ይመጣል ሲሉ አክለዋል፡፡
የቁጥጥር ስራውን ለመስራት ግን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት እና ስነምግባር በተላበሰ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተፈቀደ ቦታዎች ውጪ  ከትንባሆ ነጻ ለማድረግ መመሪያ ተግባራዊ የማድረግ እና የመቆጣጠር ስራ መጀመሩ ተነግራል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe