ባለፉት 9 ወራት በአማራ ክልል ከተገኘ 20ሺ ኪሎ ግራም ኦፓል ከ7 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ተባለ፡፡
ይሔው ተገኝቷል የተባለው 20ሺ ኪሎ ግራም የኦፓል ማዕድን በማዕከላዊ ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ነው ይፋ ያደረገው፡፡
ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኦፓል ማዕድንም ከ7ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ነው የተባለው፡፡
በክልሉ ያለውን የማዕድን ሃብት በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
ባለፈው በጀት ዓመት ከክልሉ በማዕከላዊ ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ ተልኮ ከነበረው የኦፓል ምርት ከ2ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኝቶ እንደነበር ተገልጻል፡፡

