ኪ ሀውሲንግ በተዘዋዋሪ ፈንድ የሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች የቤት ባለቤት መሆን የሚችሉበትን ኘሮጀክት ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር ከኪ ሀውሲንግ እና ከሌሎቾ ተቋማት ጋር በጥምረት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የሚችሉበትን ኘሮጀክት በዛሬው እለት በካፒታል ሆቴል ይፋ ተደርጓል።
ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ኘሮጀክቱ ይፋ በተደረገበት መርሃ ግብር ላይ የኪ ሀውሲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግሩም ይልማ እንደገለጹት ኪ ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ቤት ፈላጊዎች የቤት ባለቤት መሆን የሚያስችላቸውን የኪ- ሲ.ኤች.ኤፍ ሞዴል ማለትም ከጸሐይ ባንክና ከቡና ባንክ እንዲሁም ከቡና ኢንሹራንስ አጋርነት ያለው ፤ በአነስተኛ ከፍያና አነስተኛ ወርሃዊ ቁጠባ በመቆጠብ ከወለድ ነጻ በሆነ የረጅም ጊዜ አከፋፈል አባላቶቹ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት የዕቁብ (የተዘዋዋሪ ፈንድ) ሞዴል ተግባራዊ ያድርገ ድርጅት ሲሆን
ለአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች በአምስት ዙር ከእጣ በፊት በሚከፈል ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት መሆን የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር ኘሬዝዳንት አቶ አሸናፊ ሙልጌታ እንደገለጹት ማህበሩ ከአቢጃታ ሻላ ትሬዲንግ ሀ/የተ/የግል ማህበር ጋር ያለውን አብሮ የመሰራት የመግባቢያ ስምምነት መሰረት የማህበሩን አባላቶች ከሌሎች ቤት ፈላጊዎች በተለየ የቤት ባለቤት የሚያደግ ምቹ የሆነ የቅድመ ክፍያ እከፋፈል ስርዓት በኪ -ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊዩሽን እንዲዘጋጅላቸው ጥያቄ በማቀርብ እና ስምምነት ላይ በመደረሱ ተመዝጋቢዎች የካፒታል ቅድመ ከፍያ አካፋፈላቸውን አቅማቸው በፈቀደ በተለያዩ ጊዜያት የአከፋፈል ስርዓት በመከፈል እንዲመዘገቡ እና እጣ ውስጥ እንዲገብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምስረታውን ከዘጠኝ ወራት በፊት ያደረገው የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር የአባላቱን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሙያዊ መብት በህግ አግባብ ለማስጠበቅ፣ ለአባላቱ ጥቅም ለመስራት፣ ለሀገር እና ለአዲስ አበባ በሆቴልና በቱሪዝሙ ዘርፍ ልዩ ተሳትፎ ለማበርከት እና ዘርፉን ለማዘመን በልህቀት እየሰራ ይገኛል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe