አዲሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው ማን ናቸው?
በቫቲካን ሲቲ ሲደረግ የነበረው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ ሲጠናቀቅ ካርዲናል ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት 267ኛው የሮማን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመርጠዋል።
የጵጵስና ስማቸውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው ሆኗል። ታዲያ የእርሳቸው መመረጥ በቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ የመጀመርያው የአሜሪካ ሰው በመሆን አዲስ ታሪክ ሆኗል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው ውልደታቸው መስከረም 14 ቀን 1955 በአሜሪካ ቺካጎ ኢሊኖይስ ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከፈረንሳይ እና ካናዳ ከሆኑ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ቤተሰቦች ነው የተገኙት።
ታዲያ እኚህ አባት በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ያደጉ ሲሆን በ1982 ደግሞ የመጀመርያውን የክህነት ማዕረጋቸውን ከቅዱስ አውግስቲን ተቀብለዋል።
በሚሲዮናዊነት ወደ ፔሩ በማቅናትም በሥነ መለኮታዊ ዕውቀታቸው ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው አሁን 267ኛው የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከመመረጣቸው በፊት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ብዙ ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በፔሩ የቺክላዮ ኤጲስ ቆጶስ ሆነው አገልግለዋል።
በቆይታ ወደ ሮም የተጠሩት እኚህ አባት በዓለም ላይ ያሉትን ኤጲስ ቆጶሳት የመምረጥ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ቆይተዋል።
በዚህ አገልግሎታቸውም ዓለም አቀፋዊ ክብርን አግኝተዋል።
በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባላቸው የሥነ መለኮት እውቀት ብቻ ሳይሆን ስለ ማህበራዊ ፍትሕ በሚያደርጉት ስራ እና በሚሲዮናዊነት ስራቸው ምስጉን መሆናቸው ይመሰከርላቸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ባደረጉት የመጀመርያው ንግግራቸው “ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ካርዲናል ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት 267ኛው የሮማን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመረጡ

