ኬንያ በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አወጀች

ተሰናባቹ የጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ዕልፈት ለ3 ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን ማወጃቸውን ሲትዝን ቴሌቪዥን (Citizen TV Kenya) ዘግቧል።

ፕሬዜዳንቱ በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈት ለ3 ቀናት ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አዘዋል።

በኬንያ በቅኝ ግዛት አገዛዝ ወቅት ከተፈፀመ አሰቃቂ ታሪኮች ጋር በተያያዘ አብዛኛው ኬንያውያን ሀዘናቸውን ለመግለፅ ባይፈልጉም ኬንያታ የሶስት ቀን ሀዘን አውጀዋል ሲል የኔሽን ሚዲያው ጋዜጠኛ ኦዴኪ ጎፌሪ ፅፏል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ኬንያውያን (በንግስት ኤንዛቤት ዳግማዊት ንግስና) በቅኝ ግዛት ወቅት ከፈተፀሙ በደሎች ጋር በተያያዘ የሀዘን ቀን መታወጁን እንደማይደግፉት ፅፈው ተመልክተናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe