ክልከላ ተደርጎባቸው የነበሩ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደ

የገንዘብ ሚኒስቴር የነዳጅ ፍጆታ ለመቀነስ በሚል፤ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከሉ የሚታወስ ነው።
ይሁንና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ምክክር ካደረገ በኃላ ክልከላው እንደተነሳላቸውና ከጅቡቲ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ከውሳኔ ላይ መደረሱን አስታውቋል።
በዚሁ ዙርያ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ኃላፊዎች በተናጠል የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳታቸው ልዩነት ታይቶ ቆይቷል።
ከሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የተውጣጣ ኮሚቴ በማቋቋም ዝርዝር ግምገማዎች በማድረግ ጥያቄ የተነሳባቸው ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች የመፍትሔ ውሳኔ ላይ መደረሱን ተገልጿል፡፡
በተደረሰው ውሳኔ መሰረትም፤ የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በጅቡቲና ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ላይ የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ መፈቀዱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪ ባለፈው ዓመት ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የተገዙና በጉምሩክ ተገቢውን ምዝገባ የተደረገላቸው ተሽከርካሪዎች ጉዳይ እየተመከረበት እንደሚገኝም ተጠቅሷል።
ከጅቡቲ ወደ ድሬዳዋ መጥተው እንዲቆዩም ከውሳኔ ላይ ተደርሷል ተብሏል።
ገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ቱሪዝምን ለማበረታታት በሚል ለቱሪዝም ሥራ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ፈቅዶ የነበረ ሲሆን፤ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በተገናኘ ውዝግብ ሲነሳባቸው መቆየቱ የሚታወስ ነው።
(አሐዱ ሬዲዮ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe