ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጋራ ስምምነት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ተለያየ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጋራ ስምምነት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ተለያየ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጋራ ስምምነት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር መለያየቱን ክለቡ አስታወቀ።

ክለቡ በይፋዊ ድረገጹ ባሰፈረው መግለጫ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለክለቡ ላደረገው ትልቅ አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርቦ፣ በወደፊት የእግር ኳስ ህይወቱ መልካም ዕድል እንዲገጥመው ተመኝቷል።

ሮናልዶ በማንችስተር ዩናይትድ በቆየባቸው ጊዜያት በ346 ጨዋታዎች 145 ጎሎችን በማስቆጠር ከክለቡ ታላላቅ ተጫዋቾች በቀደሚነት የሚመደብ ነው።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል የሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከአንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ቻናል ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ “ማንችስተር ዩናይትድ ክህደት ፈፅሞብኛል” ማለቱ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe