ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከባለቤቱ ሮልስ ሮይስ መኪና ለገና በዓል ስጦታ ተበረከተለት

በአሳዛኝ ሁኔታ የኳታር ዓለም ዋንጫን የጨረሰው ኮከቡ ኳስ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከባለቤቱ የተበረከተለት የገና በዓል ስጦታ ደስታውን መልሶለታል።
የክርስቲያኖ ሮናልዶ አጋር የሆነችው ጆርጂና ሮድሪጌዝ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድን ተጫዋች ሮልስ ሮይስ መኪና ለገና በመግዛት አስደስታዋለች።
ሮናልዶ ከፒርስ ሞርጋን ጋር ያደረገውን አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ ተከትሎ ዪናይትድን መልቀቁ ይታወሳል ። ክለብ አልባው ሮናልዶ በ175 ሚሊዮን ዩሮ ወደ ሳዑዲ አረቢያ አል ናስር ክለብ ሊዘዋወር መቃረቡን ዘገባዎች ይጠቁማሉ ።አል ናስር የሳዑዲ ፕሪሚየር ሊግን 9 ጊዜ በማሸነፍ ከሀገሪቱ ትልቅ ክለቦች ሁለተኛ ደረጃን የያዘ ነው።
የአለም ዋንጫ ተሳትፎው በእንባ የተቋጨው ሮናልዶ በሞሮኮ ያልተጠበቀ የሩብ ፍፃሜ የአንድ ለዜሮ ጨዋታ ሽንፈት በኋላ ነበር።
የአምስት ጊዜ የባላንዶር አሸናፊ የ37 አመቱ ጎልማሳ ተጫዋች ሮናልዶ በገና ቀን የሮል ሮይስ ስጦታ ተሰጥቶታል ይህም በኢንሳትግራም ገፁ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ አድርጓል።
ባለቤቱ ጆርጂና የዝግጅቱን ዋና ዋና ምስሎችን ስታጋራ መኪናው ለሮናልዶ ከመሰጠቱ በፊት ልጆቻቸው ስጦታውን ሲከፍቱ አሳይታለች ።
”አንድ ልዩ የገና ምሽት እናመሰግናለን ሳንታ” በማለት ቪዲዮውን ስትለቅ በርካታ የመልካም ምኞቶች እና አስተያየቶችን ተቀብላለች።
ሮናልዶ የፈረንጆቹን አዲስ አመት የመኪና ስጦታውን ፎቶ ሲያጋራ “አመሰግናለው የኔ ፍቅር ” በማለት በደስታ ነበር።
ብዙ የሮናልዶ አድናቂዎች በኢንስታግራም የተለጠፈው ምስል ስር የምስጋና ማዕበል መልእክት ልከዋል ሮል ሮይስ መኪና ዋጋዋ 250ሺ ዩሮ ይፈጃል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe