ኮካ-ኮላ-ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ጠርሙስ ለሚሰበስቡ ማህበራት ድጎማ የሚያሰጥ ፕሮግራም አስጀመረ

ኩባንያው ለአንድ ዓመት በሚቆየው ፕሮግራሙ 10 ሚሊዮን ብር 30 ፕላስቲክ የሚሰበስቡ ማህበራት ድጎማ ያደርጋል

 ኮካ-ኮላ ቤቭሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የሚገኙ የፕላስቲክ ጠርሙስ የሚሰበስቡ ማህበራት የመሰብሰቢያ አቅማቸውን ለማሳደግ ያለመ የድጎማ ፕሮግራም ይፋ አደርገ።

በሁለት ምዕራፎች ለአንድ አመት የሚተገበረው የድጎማ ፕሮግራሙ 30 በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ጥቅም ላይ የዋሉ ፕላስቲኮችን የሚሰበስቡ ማህበራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን እስከ 10 ሚሊየን ብር ድረስ ድጋፍ ለማድረግም ታቅዷል።

ድጎማው ለማህበሮቹ በአፈፃፀማቸው መሰረት የሚሰጥ ሲሆን ሲሲቢኤ-ኢትዮጵያ ለእያንዳንዱ 1,000 ኪሎ ግራም የተሰበሰበ ፕላስቲክ የ1,000 ብር ድጎማ የሚያደረግ ይሆናል።

“ኩባንያችን በአለማችን ላይ ያለውን የፕላስቲክ መጠን ለመቀነስና ችግሩን ታሪክ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። በዚህ መነሻነት ኩባንያችን በ2030 የምናመርተውን ፕላስቲክ መጠን 100% ለመሰብሰብ እና እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል አቅደናል” ሲሉ የሲሲቢኤ ኢትዮጵያ  ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳሪል ዊልሰን በይፋ ማድረጊያ ዝግጅቱ ላይ ተናግረዋል።

Group Photo

የአዲስ አበባ ጽዳት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ “የፕላስቲክ ጠርሙሶች መሰብሰብ የኤጀንሲያችን አንዱ የትኩረት አቅጣጫ ነው። የፕላስቲክ ጠርሙስ መሰብሰብ ከተማዋን ከማጽዳት ባለፈ ለሰብሳቢዎች ዘላቂ ገቢ ይሰጣል። ከግሉ ሴክተር የሚደረገውን ይህን አይነት ድጋፍ እናደንቃለን። ከሲሲቢኤ-ኢትዮጵያ ጋር ለፕሮግራሙ ስኬት በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

ሲሲቢኤ-ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን (Polyethylene phthalate (PET)) ማሰባሰቢያ ማዕከላትን ሲቋቋሙ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን በዘርፉም ከ14,000 በላይ ሴት ፕላስቲክ ሰብሳቢዎችን በተለያዩ ፕሮጀክቶች አብቅቷል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ቆሻሻን የሰርኩላር ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚሰራውን ፔትኮ ኢትዮጵያ ሲቋቋም 150,000 ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe