ወርሃዊ ደሞዝ በአግባቡ እየተከፈለን አይደለም ሲሊ የዮቴክ ኮንስትራክሽን ሰራተኞች ቅሬታቸውን አሰሙ

ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የተቋሙ ሰራተኞች እንደሚሉት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ወርሃዊ ደሞዝ በየወሩ እየተከፈላቸው አይደለም፡፡

ሲከፈላቸው እንኳን በሁለትና ሦስት ወር አንዴ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህን ቅሬታቸውን ለተቋሙ ሀላፊዎች ቢያሳውቁም አጥጋቢ ምላሽ እንደማይሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡

ከተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞች ደሞዝ የማይከፈላቸው ደግሞ በከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና በጉልበት መሃንዲሶች መካከል ያሉት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በወርሃዊ ደሞዝ እንደመተዳደራችን መጠን ኑሯችንም እሱን ያሰላ ነው የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች፤ ክፍያው በአግባቡ አለመፈፀሙ ለከፍተኛ ችግር እንዳጋለጣቸው አንስተዋል፡፡

አሐዱ ቅሬታውን በመያዝ የዮቴክ ኮንስትራክሽን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከፍተኛ የሰው ሐይልና ፋይናንስ ኃላፊ አቶ ኪዳነማርያም አብረሃን ያነጋገረ ሲሆን ቅሬታው እውነት ስለመሆኑ አረጋግጠዋል፡፡

ለወርሃዊ ደሞዝ መዘግየቱ ምክንያት የሆነው ተቋሙም ከአሰሪዎቹ ክፍያውን በአግባቡ አለማግኘቱ ነው ብለዋል፡፡

ሰራተኞቹ ለአሐዱ ከተናገሩት ቅሬታ ሌላኛው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የጉልበት ስራ የሚሰሩት ሰዓቱን ጠብቆ ደሞዛቸውን ያገኛሉ፤ በመካከለኛ የስራ ክፍል ላይ የተሰማሩት ግን ክፍያቸው አለመፈፀሙን ያሰሙበት አቤቱታ ይገኝበታል፡፡

አቶ ኪዳነ ማርያም ግን በዚህ ሀሳብ ሙሉ በሙሉ አልተስማሙም፡፡ በጉልበት ስራ ለሚተዳደሩት በጊዜው ክፍያው ይፈፀምላቸዋል ያሉት ኃላፊው ከከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተያይዞ የተነሳው ግን ሀሰት ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ተቋሙ ከአሰሪዎቹ ክፍያው ቢፈፀምለት ችግሮቹን ለመፍታት ዝግጁ ስለመሆኑም ለአሐዱ አረጋግጧል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe