ወሲብ – ከፍላጎት ውጪ

ማንም ሰው ከፍላጎቱ ውጪ የሚያደርጋቸው ነገሮች ምቾት አይሰጡትም፡፡ ወሲብም እንዲሁ ነው፡፡ ከልብዎ ካልመጣና በፍላጎት የሚያደርጉት ካልሆነ ማስመሰል ብቻ ይኾናል፡፡ ይህ ደግሞ ዕውነተኛውን እርካታ አያስገኝም፡፡ ስለዚህ ወደ ትክክለኛው የወሲብ ግንኙነት ለመምጣት የሁለታችሁም ስሜት ተመሳሳይ የሚሆንበት ጊዜ እስኪደርስ መጠበቅ ይገባችኋል፡፡ በተለይ ሴቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ ወደ ወሲብ ሕይወት ለመመለስ አስቸጋሪ የሚሆንባቸው አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ፡፡ ስለዚህ መጠባበቅና ወደ ትክክለኛው መስመር የሚያመጣውን መንገድ መፈለግ ያስፈልጋል፡፡ ወሲብ ከፍተኛ የአእምሮ ዝግጅት የሚጠይቅ መኾኑን አይዘንጉ፡፡ ስለዚህ ለእርስዎ ፍላጎት ብቻ አጋርዎን ከማስጨነቅ በመቆጠብ አእምሯቸው ለወሲብ ዝግጁ እንዲሆን የተለያዩ አዎንታዊ ተፅዕኖዎች ያድርጉ፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የወሲብ መነሳሳት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ነገሮችንም መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ የወሲብ ፍላጎት መጥፋት በጫና ወይም በድብርት ምክንያት የሚመጣ ከሆነ ለወሲብ የሚይዙትን የተጣበበ የጊዜ ሰሌዳ ማስተካከል አንደኛው መፍትሔ መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ወሲብ የምትፈፅሙበት ቦታ ያማረ እንዲሆን ማድረግና ከትዳ አጋርዎ ጋር ለወጥ ያሉ ስፍራዎች አብሮ መጓዝ ፍላጎትዎን እንደ አዲስ ለማነቃቃት ይረዳል፡፡

የወሲብ ፍላጎት ያጡት ከልጅ መውለድ ጋር በመጡ ተደራራቢ ኃላፊነቶች ከሆነ ከባለቤትዎ ጋር በደንብ ተነጋግረው መፍትሔ ላይ መድረስ ተገቢ ነው፡፡ የቤት ኃላፊነትዎን ባለቤትዎ እንዲጋሩዎት ማድረግ፣ የወሲብ ግንኙነት ቀናችሁ ላይ አእምሮዎንና አካልዎን ዝግጁ ለማድረግ ከቤት ውስጥ ሥራዎች የሚያርፉበትን ሁኔታ ማመቻቸትና እንደ አንድ ትልቅ ተግባር ራስዎን ለወሲብ በሚገባ ማዘጋጀት ይጠበቅብዎታል፡፡

ሌላው ለወሲብ የመነሳሳት ስሜትን የሚያጠፋው ለረጅም ዓመታት አብሮ መኖርና ነገሮችን ሁሌም በተለመዱ መንገዶች ብቻ ማከናወን ነው፡፡ ስለዚህ ችግሩን ለመቅረፍ የሚችሉት ከተለመዱት የግንኙነት መንገዶች ወጣ ማለት ሲጀምሩ ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ሁሌም ፍቅራችሁ ጠንካራ ሆኖ የሚዘልቅባቸውን አዳዲስ ተግባራት ያከናውኑ፡፡ ለምሳሌ ሥጦታ ይሰጣጡ፣ አብረው ወደመዝናኛ ቦታ ይጓዙና ይዝናኑ፣ የጋብቻ ዓመታችሁንና ሌሎች አጋጣሚዎችን በመጠበቅ ሁለታችሁ ብቻ የምታከብሯቸውን በዓላት አዘጋጁ፡፡ እነኚህ የተቀዛቀዘ የወሲብ ፍላጎታችሁን ለማነሳሳት ከፍተኛ ጥቅም ይኖራቸዋል፡፡

 

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe