ወደፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ አህዮችን ለማረድ ዕቅድ እንደያዘ አሰላ የአህያ ቄራ ድርጅት አስታወቀ

አሰላ ከተማ የሚገኘው የአህያ ማረጃ ቄራ ” የአህያ ምርቶች በሙሉ ለቻይና ገበያ የሚቀርብ እንጂ አገር ውስጥ የሚቀር ምርት የለም ” አለ።

” ሮግቻንድ ” የተባለው የአህያ ማረጃ ቄራ አስተባባሪ የሆኑት ቺቺ አማን ቄራው በቀን ከ50 እስከ100 አህዮችን እያረደ ቆዳቸውን፣ ሥጋቸውን እና አጥንታቸውን ወደ ቻይና እንደሚልክ ተናግረዋል።

ድርጅቱ ከአህዮች እርድ የሚገኙት ሁሉም ምርቶች ” አንጥንታቸው እንኳ ሳይቀር ተፈጭቶ ወደ ውጪ ይላካል። እዚህ የሚቀር ምንም የለም ” በማለት ተናግሯል።

” የአህያ ሥጋ ምርት ከበሬ ሥጋ ጋር ተመሳስሎ በልኳንዳ ቤቶች ለገበያ እየቀረበ ነው ” ስለተባለው መረጃ ፤ አቶ ቺቺ ” ይህ መረጃ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ” ብለዋል።

እርሳቸው የሚያስተዳድሩት ቄራ በግብርና ሚኒስቴር ክትትል እንደሚደረግበት ተናግረዋል።

ይህ ቄራ ባለፉት 3 ዓመታት የአህያ ቆዳ፣ ሥጋ እና አጥንት ወደ ቻይና ሲልክ መቆየቱን የሚገልጹት አስተባባሪው፤ በዓመት ከአንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ እንዳስገኘ ገልጸዋል።

ቄራው ” በኢትዮጵያ የሚገኙ አህዮችን ቁጥር ያመናምናል ” በሚል ለሚነሳው ቅሬታ አቶ ቺቺ ” እኔ ይሄ እምነት የለኝም ” ብለዋል።

ለእርድ ወደ እኛ የሚመጡት አህዮች ” ከሞት የተነሱ ናቸው ” ያሉት ቺቺ  ለእርድ የሚቀርቡት አህዮች አካላዊ የጤና ጉድለት ያለባቸው እና የአገልግሎት ዘመናቸውን እያጠናቀቁ ያሉ ናቸው ፤ አገለግሎት የሚሰጡ አህዮች ለቄራው አይቀርቡም ብለዋል።

” በጣም የተጎሳቆለ አገልግሎት የማይሰጥ ወንድ አህያ ነው ወደኛ የሚመጣው። ሴት አህያ እኛ ጋር ለእርድ አይቀርቡም። ገጠር ውስጥ ሰዎችን አደራጅተን ጀርባቸው የቆሰሉ፣ እግራቸው የተሰበረ ወይም ዐይናቸው ጠፍቶ ለአውሬ የተተዉ አህዮችን ፈልገን በመኪና ጭነን ነው የምናመጣቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የአህያ ቄራ እንዲዘጋ የሚጠይቁ ድምጾች መሰማታቸው ቢቀጥልም የአህያው ቄራ ግን ወደፊት ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸውን አህዮችን በማረድ ለአገር የማስገኘውን ጥቅም ከፍ ለማድረግ አቅጄ እየሰራሁ ነው ” ብሏል።

በአሁኑ ወቅት በቀን እስከ 100 አህዮች እያረደ ሲገኝ ወደፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ አህዮችን ለማረድ ዕቅድ እንዳለው ገልጿል።

ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድልን መፍጠሩን በማመልከት፣ በዚህም በአካባቢው የተደራጁ ወጣቶች ለእርድ የሚሆኑትን አህዮችን ፈልገው በመግዛት ለቄራው ያቀርባሉ ብሏል።

የአህዮቹ እርድ መከናወን እንዲችል ከአካባቢው ማኅብረሰብ ጋር ባለፉት ሁለት ዓመታት ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውን በማንሳት ” የአካባቢው ማኅበረሰብ ቄራው የእኔ ነው ብሎ አምኖ ተቀብሏል ” ብለዋል።

የአህያ ሥጋ፣ ቆዳ እና አጥንት በቻይና ገበያ ተፈላጊ ነው።

ለዚህ ደግሞ ቁጥር አንድ ምክንያቱ የቻይና ባሕላዊ መድኃኒቶችነ ለመሥራት የሚረዳው ” ኢጂአኦ ” የተባለ ንጥረ ነገር በአህዮች ውስጥ ስለሚገኝ ነው።

በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ የሚገኘው ቄራ ከዚህ ቀደም ወደ ሥራ መግባቱን ተከትሎ ተቃውሞዎች ተሰምተው ሥራው እንዲቋረጥ ተደርጎ ነበር።

በርካቶች በባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ምክንያቶች የአህዮች መታረድን በመቃወም ድምጽ ሲያሰሙ ቆይተዋል።

በተጨማሪም አህዮች ለገጠሩ ማኅብረሰብ በተለይ ለሴቶች የሚሰጡትን ግልጋሎት እንዲሁም ሰብዓዊነትን ከግምት በማስገባት የአህያ እርድን የሚቃወሙ በርካቶች ናቸው።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe