ወደ ቻይና የተላከ ሰሊጥ መንገዱን ቀይሮ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ መሆኑ ተሰማ!

ቻይና በገቢ የግብርና ምርቶች ላይ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች፤

ቻይና በገቢ የግብርና ምርቶች ላይ አዳዲስ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧን ተከትሎ ወደ ቻይና መንገድ ጀምሮ የነበረ ሰሊጥ ወደ አአ እየተመለሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ካለፈው ታህሳስ አንስቶ የሩቅ ምስራቋ አገር ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው ቅድመ ሁኔታ በወቅቱ ባለመታወቁ ወደ አገሪቱ ተልኮ የነበረ የሰሊጥ ጭነት መንገድ እንደጀመረ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ገልጸዋል

አዲሱ አሰራር ዘግይቶ በአገሪቱ ከተገለፀ በኋላ ምርቱ እንዲመለስ መደረጉን እና የመልስ ጉዞ ላይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአዲሱ አሰራር የግብርና ምርቶች ወደ ግዙፏ ገዥ ማስገባት የሚችሉ የየትኛውም አገር ላኪዎች የራሳቸው ማቀነባበሪያ እና ማበጠሪያ ያላቸው እና ይሄንንም ማረጋገጥ የሚችሉ ብቻ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ ያሉ ላኪዎች ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት መንግስት ከቻይና ኢምባሲ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ቅድመ ሁኔታውን ማሟላት የማይችሉ ላኪዎች አቅሙ ባላቸው እና ፈቃድ ቁጥር በያዙ ላኪዎች በኩል እንዲልኩ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe