ወደ ውጭ ሀገር የሚጓዙ ሰዎች መያዝ ያለባቸው  የኮቪድ_19  ክትባት ማረጋገጫ ካርድ የቱ ነው? የጤና ሚኒስቴር ማብራሪያ

ወደ ውጭ ሀገር የሚጓዙ ሰዎች የኮቪድ_19 በሽታ መከላከያ ክትባት ከተከተቡ በኋላ ለመከተባቸው የሚሰጣቸው የክትባት ካርድ ማረጋገጫ (Authentication) መያዝ ያለባቸው ከተከተቡበት ጤና ተቋም ወይም የተከተቡበት ጤና ተቋም በሚገኝበት የክልል ጤና ቢሮ ነው፤ ሆኖም አንዳንድ መንገደኞች ለመከተባቸው ማረጋገጫ አስደርገው መጓዝ ሲችሉ ያለአግባብ ወደ ጤና ሚኒስቴር በመምጣት እየተጉላሉ ለስራም ችግር እየፈጠረ ይገኛል ይላል ጤና ሚኒስቴር፡፡

በመሆኑም ከሁሉም ክልሎች ወደ ውጭ ሀገር የሚጓዙ  መንገደኞች

  • በእያንዳንዱ ክልል ስር ባሉ ጤና ተቋማት የተከተቡ ግለሰቦች በዚያው በክልሉ ጤና ቢሮ ሄደው ለመከተባቸው ማረጋገጫ ማስደረግና መጨረስ ይኖርባቸዋል ብሏል ጤና ሚኒስቴር፤

–   በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆችና የፌደራል ሆስፒታሎች የምትከተቡ መንገደኞች በተከተባችሁበት ጤና ተቋምና ተቋሙ በሚገኝበት ክልል ጤና ቢሮ በመሄድ ለመከተባችሁ ማረጋገጫ ማስደገግ ትችላላችሁ፤

–  በተለይ እንደ አሜሪካ ወደአሉ መዳረሻዎች የምትጓዙ መንገደኞች የክትባት ማረጋገጫው ከፊርማና ማህተም አልፎ ኪው አር ኮድ (QR CODE) የሚያስፈልጋችሁ በመሆኑ ፊርማና ማህተም ካስደረጋችሁ በኋላ ለ (QR CODE) አዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ስር ባሉ ጤና ተቋማት በመምጣት ማስደረግ ትችላላችሁ ተብላችኋል፤ የተቋማትን ስም ዝርዝር ቀጣይ የምንገልጽ መሆናችን እናሳስባለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ጸጋነሽ ገድሉን (0918002002) ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡

ጤና ሚንስቴር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe