ወደ  44 ሺ የሚጠጉ ባለአክሲዮኖች በአማራ ባንክ ፈቃድ ውስጥ አልተካተቱም፤

አማራ ባንክ በኢንዱስትሪው ወጀብ ውስጥ በቀኝ ለመዋል ጠንክሮ የሚሰራ ባንክ ነው ተባለ

ወደ  44 ሺ የሚጠጉ ባለአክሲዮኖች በአማራ ባንክ ፈቃድ ውስጥ አልተካተቱም፤

በርካታ ባለአክሲዮኖችንንና ግዙፍ ካፒታል ይዞ ወደ ስራ የገባው አማራ ባንክ በዛሬው ዕለት አገልግሎት መስጠጥ  ሲጀምር 70 ያህል ቅርንጫፎችን ስራ ማስጀመሩ ተነገረ፤

የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ባንኩ  በኢንዱስትሪው ወጀብ ውስጥ በቀኝ ለመዋል ጠንክሮ ለመስራት  ወደ ኢንዱስትሪው የገባ የኢትዮጵያዊያን ባንክ ነው ብለዋል፡፡

አማራ ባንክ ራሱን በመስታወት አይቶ የመጣ ባንክ ነው ያሉት አቶ መላኩ  ከቀደሙት ታላላቆቹ ብዙ ተምሯል፡፡ ይሁን እንጂ በኢንዱስትሪው ውስጥ በየጊዜው በሚፈጠሩ በርካታ ተለዋዋጭ ገፊ ምክንያቶች የተነሳ ከፊት ለፊቱ ያለውን ተጠባቂ ውድድር እና የተከማቸ እምቅ እድልን፤ ጎን ለጎን አስቀምጦ ነው የሚጓዘው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ141 ሺህ 356 ባለአክሲዮኖች፣ በተፈረመ 6 ነጥብ 5 ቢሊዮንና በተከፈለ 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ፈቃድ ማግኘቱን ያስታወሱት ሊቀመንበሩ ወደ 44 ሺህ የሚጠጋ ባለአክሲዮኖች  በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ተቋም ቀርቦ ባለመፈረም፤፣ የተሟላ መረጃ ባለመስጠት እና በውጭ ምንዛሬ መግዛት ሲገባ በብር በመግዛት  በፍቃዱ ውስጥ አልተካተቱም ብለዋል፡፡

ዶክተር ይናገር ደሴ ሰሞኑን ንግድ ባንኮች ከጎጥ፣ ከብሄረሰብ እና ሐይማኖት አስተሳሰብ እንዲወጡ መምከራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe