ወጣቱ ድምጻዊ ምስክር አዋል የአልበም ስራው ሳይጠናቀቅ ከፈቃዱ ውጪ ለህዝብ እንደደረሰ ገለጸ

ከ90ዎቹ ተወዳጅ ድምጻዊያን መካከል አንዱ የሆነው ምስክር አዋል የአልበም ስራው ሳይጠናቀቅ ከፈቃዱ ውጪ ለህዝብ እንደደረሰ ገለጸ፡፡ ከሦስት ሳምንት በፊት ልቻለው የተሰኘውና አልተጠናቀቀም የተባለው ስራው ለህዝብ ደርሷል፡፡

ምስክር ኢትዮጽያ፡እያመነሽን የመሳሰሉ ስራዎችን በልጅነቱ ለህዝብ አድርሶ በጣም ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻለ ድምጻዊ ነው፡፡

ምስክር አወል የሙዚቃ ስራውን የጀመረው በህጻናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ነው፡፡

ትላንት ምሽት በሰይፉ ሾው ላይ በእንግድነት ቀርቦ አዲሱ የተለቀቀው የሙዚቃ አልበሙ ሳይጠናቀቅ እንደሆነ ለህዝብ በመንገር አንጋፋ ሙዚቀኛዎችንና አድማጭን ስለሁኔታው በመግለጽ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ምስክር በቃለ ምልልሱ ወቅት ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት ከአንድም ሁለት ጊዜ ቀረጻውን እያቆራጠ ሲወጣም ተስተውሏል፡፡

ይህ ተወዳጅ ድምጻዊ ምስክር አወል ከሰይፉ ጋር የነበረው ቆይታ በእንባ እና በመረበሽ የታጀበ ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ብዙ ደከምኩበት ያለው የሙዚቃ ስራው ሳይጠናቀቅ ለህዝብ መድረሱና፤ከግል ህይወቱ ጋር የተገናኙ አንዳንድ ነገሮችም ሆድ እንዲብሰው አድርገውታል፡፡

 

በቀጣይም ይሄው አዲሱ ስራው እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በርግጠኝነት ባይናገርም፤ተሰተካክሎ ሊቀርብ የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል ጠቆም አድርጓል፡፡

ምስክር በዚህ ስዓት ከሙዚቃ ስራው በተጨማሪ በፈርኒቸር ስራ ተሰማርቶ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጻል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe