ወጣት ሰሚራን በጭካኔ የደበደቡ ሁለት ፖሊሶች 3300 ብር ብቻ እንዲቀጡ ተወሰነ

ባለፈው መስከረም ወር ማለቂያ ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሚካኤል አደባባይ አካባቢ በአነስተኛ ንግድ ስራ ላይ ተሰማራች ወጣት ሰሚራ የተባለች  የልጅ እናትን በጭካኔ የደበደቡ ሁለት ፖሊሶች  ፍርድ ቤት ቀርበው መቀጣታቸው ታወቀ፡፡

ምክትል ኢንፔክተር ጃፈር አሊ እና ኮንስታብል መስፍን በለጠ የተባሉ ሁለት ፖሊሶች የልጅ እናት የሆነችውን ወጣት ሰሚራን ከልጇ ፊት ሲደበድቡ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ መገናኛ ብዙብሃን መተላለፉን ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከፖሊስ ይህንኑ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተላለፈ ቪዲዮ ተመልከቶ በ24 ሰዓት ውስጥ ሁለቱን ፖሊሶች በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ያደረገ ሲሆን ለሚመለከተው ንፋስ ስልክ ላፍቶ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በማቅረብ እያንዳንዳቸው በ3300 ብር ብቻ መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ‹የቸገረን ነገር› ፕሮግራም ላይ ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፅሙ የታዩት እነዚህን ሁለት ፖሊሶች ላይ ተሰጠው ፍርድ በቂ አይደለም ብለን ወስደናል ያሉት ኮማንደር ፋሲካ ኮሚሽኑ ለሌሎች ፖሊሶች ማስተማሪያ እንዲሆን ሁለቱንም ፖሊሶች ከስራ ማባረራቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ብቻ በ171 የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶች ከስነ ምግባር ውጭ በመንቀሳቀሳቸው ምክንያት  አቤቱታ የቀረበባቸው ሲሆን 29 ያህሉ በከፍተኛ የስነ ምግባር ችግር ከስራ መባረራቸው ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe