ወጣቷ ሚሊየነር የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለቤት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአራት ሚኒስትሮችን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን የሴቶች የህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እንዲሰሩ የተሾሙት ወ/ሮ ፈልሰን አብዱላሂ በዕድሜ ትንሷ ሚኒስትትር መሆናቸው ታውቋል፡፡
የ29 ዓመቷ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈልሰን ድሬዋዳ ተወልደው አዲስ አበባ ያደረጉ የሶማሌ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ እስከ ለውጡ መምጣት ድረስ ቋሚ መኖሪያቸው በእንግሊዝ ሀገር እንደሆነ ታውቋል፡፡ ከለውጡ በኋላ ወደ ሀገር ቤት በመግባት ነበድ የተባለ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያ በጂግጂጋ ከተማ በማቋቋም ለውጡን የሚደግፉ ዘገባዎችን በማሰራጨት ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ወ/ሮ ፊልሰን ባለትዳርና አንድ ልጅ እናት ሲሆኑ በትምሀርት ዝግጅታቸው ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ከእንህግሊዝ ሀገር ሃርቨር ሸር ዩኒቨርሲቲ በኮሚዩኒኬሽን ሳይንስ እና በስነ ልቦና ሁለት የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው፡፡ የማስተርስ ዲግሪያቸውንም ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በስነ ልቦና ማግኘታቸውን ለምክር ቤቱ የቀረበው የህይወት ታሪካቸው ሰነድ ያሳያል፡፡ ሚኒስትሯ ወደዚህ ከፍተኛ የሀላፊነት ቦታ ከመምጣታቸው በፊት የሰላም የዲሞክራሲና የእኩልነት ድምጽ ሊሆን የሚችል ነበድ ተባለ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ያቋቋሙ የመጀመሪያዋ ሴት መሆናቸውን ለምክር ቤቱ የተገለፀ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት ስለመሰረቱት የቴሌቪዥን ጣቢያ የካፒታል ምንጭ ምን እንደሆነ በምክር ቤት አባላት የተነሳ ጥያቄ የለም፡፡
በእንግሊዝ ሀገር በትምህር ላይ መቆየታቸው ተገለፁት ወ/ሮ ፈልሰን ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለቤትና ስራአስኪያጅ ናቸው፤ ወ/ሮ ፈልሰን በሶማሌ ክል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የሚመራው የብልፅግና ፖርቲ የሶማሌ ቅርንጫፍ አባል ሳይሆኑ መሾማቸው ያነጋገረ ሲሆን ከአቶ አህመድ ሽዴ ቀጥሎ ከፍተኛው የክልሉ ተሻሚ መሆናቸው ታውቋል፤
ወ/ሮ ፊልሰን ከሳምንታት በፊት የሰላም አምባሳደር ተደርገው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተሸሙ ስድስት ግለሰቦች መሀከል አንዷ ሲሆኑ የሱማሌና የኦሮሞ ወጣቶችን ኮንፈረንስን ሲያዘጋጁ የክብር እንግዳው የኦኤምኤን ቴሌቪዥን ባለቤት አቶ ጃዋር መሀመድ እንደነበር ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe