የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ዩናይትድ ስቴትስ አሁንም በሆን ጦርነቱ እንዲቋጭ ለማድረግ ዝግጅቱም ሆነ ፈቃደኝነቱ አላት ብለዋል፡፡
ዋሽንግተን የዩክሬኑን ጦርነት ለማቆም በሚደረገው ሂደት ላይ መሳተፏን እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ የዚህን ጦርነት ፍጻሜ ለማፋጠን አቅሟ የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጅ ናት፤በሆነ ወቅትም ይህ ዕድል ይፈጠራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን በማለት ሩቢዮ ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ ከኢራን ጋር ወደ ጦርነት ከገባችበት የካቲት ወዲህ የዩክሬኑን ጦርነት በስምምነት እንዲጠናቀቅ የማድረጉ ሂደት በብዙ የተገታ መስሎ ቀጥሏል፡፡ በእነዚህ ወራት ውስጥም እጅግ ከፍተኛ የተባሉ ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ዘገባዎች በተለያዩ ጊዚያት ወጥተዋል፡፡ በሌላ በኩል ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ላይ መጠነ-ሰፊጥቃት ልትሰነዝር መሆኑን አስጠነቀቀች፡፡ ይህንን ተከትሎም ኪየቭን ለቃችሁ ውጡ የሚል መልዕክት ሞስኮ አስተላልፋለች፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ላይ ጥቃት ልትሰነዝር መሆኑን በመግለጽ፤በከተማዋ የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች እና ዲፕሎማቶች በአስቸኳይ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች፡፡
የሩሲያ መንግስት የውጭ ዜጎች እና ዲፕሎማቶች በተቻላቸው ፍጥነት ኪየቭን እንዲለቁ ትዛዝ የሰጠ ሲሆን፤የዪክሬን ዜጎችም ከአስተዳደር እና ከወታደራዊ ህንጻዎች እንዲርቁ ጠይቋል፡፡
የሩሲሰ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ከሆነ አዲሱ ጥቃት በዋናነት የውሳኔ መስጫ ማዕከላትን፡የወታደራዊ ዕዝ ጣቢያዎችን እና የሰው አልባ አውሮፕላን ማምረቻ ቦታዎችን ያነጣጠረ ይሆናል፡፡
ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰማው ሩሲያ ዕሁድ እለት ከፍተኛ የጠባለ ጠወቃት ካደረሰች በኋላ ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሉሃንስክ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ላይ ለደረሰው ጥቃት አጸፋዊ እርምጃቸውን እንደሚያጠናክሩ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

