ዓለም አቀፋዊ የኢትዮጵያ ማኅበረሰባዊ ድርጅቶች መንግስት እነ አቦይ ስብሃትን መፍታቱን ተቸ

ውሳኔውን እንዲሽርም  ጠይቋል፤

የኢትዮጵያ መንግስት በሚሰራው ሥራ ሁሉ ግልፅነት እና ተጠያቂነት እንዲኖረው ዓለም አቀፋዊ የኢትዮጵያውያን ማኀበረሰባዊ ድርጅቶች ሲጠይቅ በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሃት  አመራሮችን መፍታቱን ተችተዋል፤

ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገኙ 21 ማኀበረሰባዊ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ መንግስት ከአሁን በፊት ተፈፀሙ ላሏቸው ጥፋቶች እና ስህተቶች ዕውቅና ሰጥቶ ኃላፊነት እንዲወስድና ይቅርታ እንዲጠይቅ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከአመት በፊት ጦርነቱን በበላይነት ባጠቀቀ ማግስት ከመቀሌ  ጠቅልሎ መውጣቱን የተቸው መግለጫው አሁንም ወራሪውን የህወሃት ሀይል ከአማራና ከአፋር ክልል ቢያስወጣም ወደ ትግራይ  ገብቶ አጥፊውን አመራር ከማጥፋት ይልቅ ጉዞውን መግታቱ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል ብሏል፤

መንግስት በተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የፈረጀው  የአሸባሪውን የጥፋት ሀይል ከፍተኛ አመራሮችን ያለምንም ማብራሪያ መፍታቱ በዲያስፖራ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩን  አብራርቷል፤

መንግስት ሰሞኑን የወሰደውን እርምጃ እንዲሽርና የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ የሚጠይቀውን ይህንን መግለጫ ለመገናኛ ብዙሃን ከማሰራጨት በተጨማሪ ለኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴና ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም ለአማራና ለአፋር ክልል ፕሬዚዳንዳቶች መላካቸው የዓለም አቀፋዊ የኢትዮጵያውያን ማኀበረሰባዊ ድርጅቶች ሰብሳቢ ኢንጂነር እስቄኤል እስክንድር ለዶቼቬሌ ተናግረዋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe