የሃይንከን ኢትዮጵያ ደራሽነት!

ማንኛውም የቢዝነስ ስራ በእውቀትና በትጋት ብሎም ማህበረሰቡን በማገዝ ላይ ሲደገፍ ኢንቨስትመንቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያስችላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ‘’የምናድገው ከኢትዮጵያ እና ከማህበርሰቡ ጋር ነው’’ የሚለው ሃይንከን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ውስጥ እያስመዘገበ ካለው ስኬት ጎን ለጎን እያከናወናቸው ያለው ከልብ የሆኑ ማህበራዊ አገልግሎቶች ሰፊ መሠረትና ተደራሽነት ያላቸው ናቸው።

ሃይንከን የኢትዮጵያን የቢራ ገበያ የተቀላቀለው በ2003 ዓ.ም ሲሆን፣ በመንግስት የተያዙ ሁለት የቢራ ፋብሪካዎችን በመግዛት ነው ስራውን የጀመረው። እነዚህም በምስራቅ ኢትዮጵያ በሐረሪ ክልል ሐረር ቢራ ፋብሪካንና በምዕራብ  ደግሞ በበደሌ ከተማ በደሌ ቢራ ፋብሪካ ሲሆኑ አዲስ አበባ ላይ ደግሞ በቂሊንጦ ሶስተኛውን ቢራ ፋብሪካ ገንብቷል። በነዚህም ሶስት ፋብሪካዎች ሃይንከን፣ ዋልያ፣ ሐረር፣ በደሌ ስፔሻልና በደሌ፣ በክለርና ሶፊ ማልትን የሚያመርት ሲሆን፤ በቅርቡ ደግሞ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ብቅል ቀመስ ሃይል ሰጪ መጠጥ ብርታትን ለገበያ አቅርቧል።

ቢራችንን የምናመርተው የአገራችን አርሶ አደሮች ባመረቱት ገብስ ነው

የእርሻው ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየገጠመው ያለው ጉዳይ ምርታማነትን በመጨመር እንዴት ያለውን የምግብ ፍላጎት ዘላቂ በሆነ መንገድ እናርካ የሚለው ነው፡፡ በመሆኑም ዘላቂነት ያለው አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ ለድህነት ቅነሳም ሆነ ለምግብ ዋስትና ጥረቶች የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

በመሆኑም ሃይንከን ሥራውን ማከናወን የሚፈልገው የአርሶ አደሮች እና የማህበረሰቡ የኑሮ ደረጃ በሚሻሻልበት፣ የአካባቢ ሁኔታ በሚጠበቅበት እና የጥሬ ዕቃ አቅርቦቱ አስተማማኝ በሆነ መልኩ በሚቀርብበት ሁኔታ ነው፡፡

የአገር ውስጥ የቢራ ገብስን መጠቀም ላይ ባተኮረው በዚህ ፕሮጀክት አነስተኛ የእርሻ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች ምርት እንዲጨምር በማድረግ ከውጭ የሚገባውን ምርት የመቀነስ ብሎም ሙሉ ለሙሉ የመተካት ስራ ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ማድረጉ አርሶ አደሮቹ ከማሳቸው ላይ የሚያገኙት ምርትና ገቢ እንዲጨምር ከማስቻሉም በተጨማሪ ድህነትን ለመቀነስ እና በምግብ እህል ራስን ለማስቻል የሚደረገውን ጥረትም በእጅጉ ያግዛል፡፡ ከሁሉም በላይ የኢኮኖሚ አቅማቸው እንዲዳብር በማድረግ የራሳቸው እና የቤተሰባቸው የኑሮ ደረጃ ከፍ እንዲል አስችሏቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ሃይንከንንም ጠቅሟል፡፡ ከውጭ ሲያስገባ የሚከፍለውን ግብር ከማስቀረቱም በተጨማሪ ዘላቂነት ካለው ምንጭ ምርቱን ለማግኘት አስችሎታል። እንዲሁም ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ችግሮችንም ያስቀራል፡፡

ሃይንከን ኢትዮጵያ ይህን ፕሮጀክት የጀመረው በ2013 (እኤአ) ሲሆን፤ አጀማመሩም ከአራት የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች ጋር የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ ጥምረትን በመመስረት ነበር፡፡ የእርሻ ቴክኖሎጂን በማስፋፋት የማህበረሰብ ገቢን ማሳደግ የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት ከእርሻ ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ እርሻ ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በጥምረት የሚሠራበት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የቢራ ገብስ በምርት ብዛትና ጥራት እንዲያድግ ለማድረግ የታለመ ሲሆን፤ በተጨማሪም የአርሶ አደሮች ገበያ የማግኘት ሁኔታንም የሚያሻሽል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ፕሮጀክቱ ለ70,000 አርሶ አደሮች ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የአርሶ አደሮቹ የምርት መጠንም በሚያስገርም ሆኔታ በማደግ ከዚህ ቀደም በአንድ ሄክታር 2.4 ቶን ያገኙ የነበረውን አሁን በሄክታር 5 ቶን እንዲያገኙ አስችሏል፡፡  የብዙዎቹ አርሶ አደሮች እና ቤተሰባቸው ህይወትም ለውጥ እየታየበት ነው፡፡ ይህን በማድረጉም ሃይንከን ኢትዮጵያ አምስተርዳም ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ የዘንድሮውን አለም አቀፍ ሽልማት አግኝቷል። ይህን ተከትሎም ሃይንክን ለዚህ ክብር ያበቁትን አርሶ አደሮች መልሶ ሸልሟቸዋል።

Ato sisaye meskash

“የእኛ ቡና ገብሳችን ነው”በገብስ እርሻ ስራ ላይ የተሰማሩት ተሸላሚ አርሶ አደር  ሲሳይ መካሻ እና ባለቤታቸው ወ/ሮ ዴንሲ አብዲ በዚሁ መርሃ-ግብር የታቀፉና በአርሲ ዞን ሊሙ ቢልቢሎ ወረዳ ነዋሪ ናቸው።   አቶ ሲሳይ እንደሚሉት ሃይንከን ኢትዮጵያ ወደ ዞናቸው መጥቶ ትራቭለርና ግሬስ የተሰኙ ምርጥ ዘሮችን እንዲጠቀሙና የእርሻ ስራቸውን እንዲያዘምኑ ስልጠና ካገኙ በኋላ በሄክታር ቀደም ሲል ያገኙ የነበረውን 25 ኩንታል ከእጥፍ በላይ አድጓል።

የምዕራብ አሩሲ ዞን ሻሸመኔ ወረዳ ሁርሳ ቀበሌ  ነዋሪ የሆኑት ሌላው ተሸላሚ አርሶ አደር አቶ መርጋ ገመዳ  ደግሞ ሃይንከን ኢትዮጵያ ባቀረበው የምርጥ ዘር፣ የፀረ አረምና ፀረ ተባይ መከላከያ ስልጠና ታግዘው የቢራ ገብስ በማምረታቸው ውጤታማ አርሶ አደር መባላቸውን ይናገራሉ፡፡

አቶ መርጋ እንደሚሉት በስልጠናውና በግብርና ባለሙያዎች ያልተቋረጠ ክትትል ታግዘው በሄክታር የሚያገኙትን የቢራ ገብስ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችለዋል።ከሰባት ዓመታት በፊት በተመሳሳይ ማሳ ከፍተኛ የተባለውን በሄክታር 30 ኩንታል ብቻ  ማግኘታቸውን ያስታውሳሉ። ’’ማየት ማመን ነው’’ የሚሉት አቶ መርጋ በቅርቡ ምርቱን ለመሰብሰብ እየተዘጋጁ ያሉበትን የገብስ ማሳ እያሳዩ ‘’ምንም አልተገኘም ከተባለ ከዚህ እርሻ በሄክታር ከ70 ኩንታል በታች አይገኝም ብዬ አስባለሁ’’ ይላሉ። አቶ መርጋ ሞዴል አርሶ አደር በመሆናቸው ሰልጥነው በተግባር ያገኙትን ለውጥ በመስመር ስለ መዝራትና ስለ ፀረ አረም መድሃኒት አጠቃቀምን ጨምሮ ልምዳቸውን በስራቸው ለታቀፉ ለሌሎች አርሶ አደር ማህበራት ማካፈል ጀምረዋል።

ኢትዮጵያ ለቢራ ምርት የሚሆን ገብስ በበቂ ሁኔታ ማምረት ባለመቻሏ ለዓመታት ብቸኛ የነበሩት የአሰላ እና የጎንደር ብቅል ፋብሪካዎች ከውጭ ሀገር ገብስ በብዛት ያስገቡ ነበር። ሃይንከን ኢትዮጵያ ይህንን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት ከገብስ አምራች አርሶ አደሮች ጋር በነደፈውና ተግባራዊ ባደረግው የቢራ ገብስን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ፕሮጀክት በጥቂት ዓመታት  ኢትዮጵያ የቢራ ገብስ ፍላጎቷን ከማሟላት አልፋ ለውጭ ገበያ ታቀርባለች። ይህን የአገር ውስጥ ምርት መጨመርን ተከትሎ የብቅል ፋብሪካዎችም ከሁለት ወደ አራት አድገዋል።

ማህበራዊ ድጋፎች ደራሽ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት

መኖሪያ ቤት ኢትዮጵያ ውስጥ አንገብጋቢና  በጣም  መሰረታዊ ጉዳይ ነው። 65 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚኖረው የመኖሪያ ቤት ደረጃን የማያሟሉ መጠለያዎች ውስጥ ነው።ስለሆነም ይህንን የአገሪቱንና የማህበረሰቡን አንገብጋቢ ጉዳይ መፍታት ለሃይንክን ኢትዮጵያ ወቅታዊና ወሳኝ ጉዳይ ሆኖ ቀርቧል።

ቀደም ሲል የነበረው ቤት መፍረሱ በፊትና በኋላ

ከዚህም በመነሳት “ደራሽ” የተሰኘ የችግረኛ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ግንባታ መርሃ-ግብር ክ2013 ዓ/ም በመተግበር ላይ ይገኛል። እስክአሁን በ”ደራሽ” ፕሮጀክት  ለ145 አባወራዎችና ለ700 የሚደርሱ የቤተሰብ አባሎቻቸው ደረጃቸውን የጠበቁ የመኖርያ ቤቶች  አስረክቧል።  እነዚህ መኖርያ ቤቶች ክ28 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ሲሆን በግንባታው ሂደትም ለ450 ወገኖች የስራ ዕድል ፈጥሯል።

የሃይንከን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ፣ በደሌ እና ሐረር ለ120 ወገኖች የስራ ዕድል የፈጠረውን ፕሮጀክት በማጠናቀቅ ላይ ነው። የአዲስ አበባው ፕሮጀክት ችግረኛ ሴቶችን ያቀፈ ሲሆን፤ የስራ እድሉ የተፈጠረላቸው ሴቶችም እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ፓድ አምርቶ በመሸጥ ላይ የሚሰማሩ ናቸው።

ስራ ፈጠራው በሴቶች ላይ ያተኮረው የሴቶች ስራ አጥነት በደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ስለሚያሳድር እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ አፈፃፀም እና ማህበራዊ መረጋጋት ላይም የጎላ ሚና ስለሚኖረው ነው፡፡

የፕሮጀክት ትግበራው በአዲስ አበባ በሶስት ክፍለ ከተሞች ውስጥ ለሚኖሩ በአጠቃላይ ለ40 ሴቶች እድል የተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ከቂርቆስ (15)፣ ከቂሊንጦ (20) እና ክቀጨኔ (5) የተውጣጡ ናቸው።

የግብር አስተዋጽኦ

ሃይንከን የፕላቲኒየም ደረጃ ግብር ከፋይ ተሸላሚ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በአገሪቱ ካሉ ግብር ከፋዮች መካክል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው። ባለፉት አራት ተከታታይ አመታት  የፕላቲኒየም ደረጃ ታክስ ከፋይ በመሆን በፌደራል መንግስትና በግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት እውቅና አግኝቷል።  ሃይንከን ባለፈው የዓመት ብቻ  6.1 ቢሊዮን ብር ግብር ከፍሏል።

የአካባቢ ጥበቃ

በሃይንከን ኢትዮጵያ የምርት ሂደት ውስጥ አረንጓዴ አካባቢን መፍጠር ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ተግባር ነው፡፡ ሃይንከን ኢትዮጵያ ለማምርት የሚጠቀመውን ውሃ ዘመናዊ ማሽኖችን በመጠቀም ክመቆጠብ በተጨማሪ በጥቅም ላይ የዋለን ውሃም በማጣሪያ ማዕከሉ በማጣራት አካባቢው ላይ ምንም ዓይነት ብክለት በማያደርስ መልኩ ያስወግዳል።  በአካባቢው ያለውን የአየር ንብረት ለማሻሻልና የከርሰ ምድር የውሃ ክምችትን ለማሳደግ ዛፍ በመትከል እና የውሃ ምንጮችን በማጎልበት ህይወትን ይመልሳል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ እስከአሁን በአዲስ አበባ፣ ሃረርና በደሌ በድምሩ 80ሺ ችግኞች ተተክሏል።

ሃይንከን ስፖርት እና ጤናማ ህይወት

ሃይንከን ኢትዮጵያ እግር ኳስ የኢትዮጵያውያን ተወዳጅ ስፖርት መሆኑን ከግምት በማስገባት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ጎን ቆሟል፡፡

ዋልያ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ብርቅዬ የዓለማችን የዱር እንስሳ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም የተሰየመው በዚሁ ስም ነው። ዋልያ! በመሆኑም ሃይንከን በዚሁ ብርቅዬ እንስሳ ስም የሰየመውን ተወዳጅ ቢራ ‹ዋልያ ቢራ!› ይፋ ካደረገበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያውያን ኩራት የሆነውን ብሔራዊ ቡድን በ64 ሚሊዮን ብር ደግፏል። ሶፊ በተሰኘው ምርቱም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንንም በ30 ሚሊዮን ብር ይደግፋል።

የሠራተኞች ስልጠናና ቅጥር

ሃይንከን በኢትዮጵያ ከ28 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት ያደረገ ሲሆን ከ2ሺ በላይ ሠራተኞችአሉት። ሃይንከን ኢትዮጵያ አዳዲስ የሚቀጠሩና ድርጅቱን የሚቀላቀሉ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ነው የሚቀጥረው። በተለይም አዳዲስ ተመራቂዎች ከዩኒቨርሲቲዎች ሲወጡ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ቅኝት በማካሄድ  በማኔጅመንት የስልጠና ፕሮግራሞች ውስጥ እንዲያልፉና የስራ ዕድል እንዲያገኙ ያደርጋል።

የሃይንከን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳሬክተር የሆኑት ሂውበርት ኢዜ ‘’ግባችን የማህበረሰቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የያዘውን ሰፊ የገበያ ድርሻ ይበልጥ በማሳደግ መሪነቱን ማስቀጠል ነው’’ ይላሉ።  ሂውበርት ኢዜ ‘’ለማህበረሰቡ የምናደርገው ድጋፍና ለአካባቢ የምንሰጠው ትኩረት የስራችን ዋና አካል ነው’’ እንዳሉት ሃይንከን ኢትዮጵያ በተወዳጅ ምርቶቹ እና ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ በማደግ ጥረቱ ይዘልቃል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe