የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩ እና ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን “በሽብርተኝነት” ሊከሳቸው መሆኑን ዐቃቤ ህግ አስታወቀ

ተጠርጣሪዎቹ የፌደራል መንግስት “ከስልጣን ስለገፋን” በማንኛውም መንገድ እንዲወገድ መደረግ አለበት በማለት ሚስጥራዊ ወታደራዊ ዕዝ ማቋቋማቸውን ዐቃቤ ሕግ የፖሊስ የምርመራ መዝገብን ጠቅሶ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ገልጿል፡፡

በቀዳሚ ምርመራ የምስክርነት ቃላቸውን የሚሰጡ 83 ሰዎች መዘጋጀታቸውንም ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤት አብራርቷል፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት ወ/ሮ ሕርቲ ምህረተአብ እና የክልሉ መንግስት አማካሪ የነበሩት ወልደጊዮርጊስ ደስታ ፣ በቂ ዋስ ጠርተው ቢለቀቁ ዐቃቤ ሕግ እንደማይቃወም አስታውቋል፡፡

ሌሎች ተጠርጣሪዎች ግን ሕገመንግስታዊ ስርዓትን በኃይል መናድ ፣ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ናቸው በሚሉ እና በሌሎች ወንጀሎች ጠርጥሮ እንደሚካሳቸው ለፍርድ ቤት ገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ እንዲዘጋለት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

የተጠርጣሪ ጠበቆች ሂደቱን በመቃወም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ማቅረባቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe