የህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ህጻናቱን ለሞት የሚዳርግ የምግብ እጥረት መፈጠሩ ተሰማ

ባለባቸው የምግብ እጥረት የተነሳ ህጻናት ለሞት ተጋላጭ የሆኑባቸው የህጻናት ማሳደጊ መኖራቸውን በክትትሌ ደርሼበታለሁ ሲል የኢትዮጽያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡

ኮሚሽኑ ይህንኑ በተመለከተ ከዚህ ቀደም የሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች መፈጸም አለመፈጸማቸውን መገምገሙንም አስረድቷል፡፡

በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት መካከል በአንዳንዶቹ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የቀጠሉባቸው ተቋማት መኖራቸውን የኢትዮጽያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ ገልጻል፡፡

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ፡በአዳማ፡በሀረር፡ በሻሸመኔና በወላይታ ከተሞች በሚገኙ 21 የህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት ከሰብዓዊ መብት ጥበቃ አኳያ ከዚህ ቀደም የተሰጣቸው ምክረ ሃሰቦች ምን ያህሉ ተፈጽመዋል የሚለውን እና ግኝቶች ላይ ተወያይቷል፡፡

በዚህም የተሻሻሉ ጉዳዮ ቢኖርም አሳሳቢነታቸው የቀጠለውን ለይቶ ምክረ ሃሳቦችን ሰጥቷል፡፡

አሳሳቢነታቸው ከቀጠሉት መካከል የምግብ እጥረት በመኖሩ የህጻናቱ የጤና መብት ተጥሷል ተብሏል፡፡

በምግብ እጥረት ምክንያት ህጻናትን እስከ መሞት የሚያደርሱ ሁኔታዎች ላይ እንደሚገኙና ከስድስት ወር በታች የሆኑ ህጻናት ለዚህ አደጋ ተጋላጭ እንደሆኑ ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በእነዚሁ ማሳደጊያ ተቋማት ከዚህ ቀደም ክፍተት የታየባቸው ጉዳዮች አሁን ላይ መሻሻል መሳየታቸውም ተነግሯል፡፡

መሻሻል ከታየባቸው ጉዳዮች መካከል አካል ጉዳተኛ ህጻናትን ማካተት አንዱ ሲሆን የህጻናቱን መረጃ በአግባቡ ሰንዶ ማስቀመጥ የሚለው ይገኝበታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe