የመስከረም ወር የዋጋ ግሽበት ከአምናው በ34.8 በመቶ ጭማሪ አሳየ

በመገባደድ ላይ ባለው የመስከረም ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከአምናው በ34.8 በመቶ ከፍ ማለቱ ተነገረ፡፡
የዋጋ ግሽበት ምጣኔው በተለይ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ያሳየው ጭማሪ ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ42 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
በተለይ በዳቦ እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ እንደቀጠለ ነው ያለው ኤጀንሲው የሩዝ፣ የእንጀራ፣ የዳቦ፣ የጤፍ፣ የስንዴ፣ የማሽላ፣ የገብስ፣ የስንዴ ዱቄት፣ የፓስታና የመኮሮኒ ዋጋ በፍጥነት መጨመሩን ከላከልን መረጃ ተመልክተናል፡፡
በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች ዋጋም ከአምናው በ25.2 በመቶ መጨመሩን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ ያመለክታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe