የመንገድ ደህንነት ትምህርት በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካቶ ሊሰጥ ነው

የመንገድ ደህንነት ትምህርት በአገር አቀፍ ደረጃ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ተካቶ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ሊሰጥ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህንንም ምክንያት በማድረግ የመንገድ ደህንነት ስርዓተ ትምሀርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተከናወነ ነው።
የመንገድ ደህንነት ትምህርት በ11 የትምህርት አይነቶች ላይ ተካቶ የሚሰጥ ይሆናልም ተብሏል።
የመንገድ ደህንነት ትምህርቱ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ መካተቱ በታዳጊዎች ላይ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ትራንስፖርት ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን እንደሚተገበር ታውቋል።
የመንገድ ደህንነት ትምህርት በ2014 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በ50 ሺህ 816 ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።
ትምህርቱ 34.1 ሚሊየን ተማሪዎች የሚማሩት ሲሆን ከተማሪዎቹ ጎን ለጎን 22 ሚሊዮን ጎልማሶች ትምህርቱን እንደሚወስዱ ተገልጿል።
ባለፉት ሶስት አመታት ብቻ 1 ሺህ 915 ወጣቶች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። ?EBC/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe