የመንግሥት ከፍተኛ ተሿሚ ባለሥልጣናት በስማቸው እና በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ባለቤትነት የተመዘገቡ የንግድ ድርጅቶችን ወይም የአክሲዮን ድርሻዎችን እንዲያቋርጡ ሊደረግ ነው

የፌዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የመንግሥት ከፍተኛ ተሿሚ ባለሥልጣናትን በስማቸው እና በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ባለቤትነት የተመዘገቡ የንግድ ድርጅቶችን ወይም የአክሲዮን ድርሻዎችን እንዲያቋርጡ ወይም ለሌላ እንዲያስተላፉ የሚያስገድድ ደንብ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ረቂቅ ደንቡ የመንግሥት ተሿሚዎች በሥራቸው ምክንያት ከሚከሰት የጥቅም ግጭት መራቅ አለባቸው ይላል።
በረቂቅ ደንቡ ክፍል ሦስት ውስጥ ባለስልጣናት የጥቅም ግጭትን ለመከላከል እና ለማስወገድ የጥቅም ግጭት መነሻ ከሆነው የግል ድርጅት ድርሻውን እንዲያስተላለፍ ወይም እንዲያቋርጥ፣ በግል የያዘውን ድርጅት በውክልና እንዲያሠራ እና ካፒታሉንና ትርፉን ማዘዝ በማይችልበት ሒሳብ ቁጥር እንዲያስቀምጥ እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት በቦርድ አባልነት ፣በዳይሬክተርነት የያዘውን ኃላፊነት እንዲለቅ የሚያደርግ ነው።

አንድ የሕግ ባለሙያ ለDW በሰጡት አስተያየት ይህ ረቂቅ ደንብ ግለሰቦች ባለስልጣን ስለሆኑ ብቻ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ያለ አግባብ የሚነካ ነው ብለዋል። የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ – ሙስና ኮሚሽን ከዚህ በፊት ባለሥልጣናቱ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጀምሮት የነበረውን ሥራ ማስቀጠል ሲገባው ሌላ ረቂቅ ሕግ ይዞ መምጣቱ የባለስልጣናቱን ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚጋፋ ነው ያሉት እኚሁ የሕግ ባለሙያ ሙስናን ለመከላከል ዋናው መፍትሔ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው ብለዋል ሲል DW ዘግቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe