የመከላከያ ሠራዊት በአብዛኛው ከአንድ አካባቢ በመጡ ሰዎች የተሞላ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ በመከላከያ ሠራዊት ሁሉም አዛዦች የትግራይ ተወላጆች እንደነበሩም አስታውቀዋል፡፡መከላከያና ደህንነት የነበሩ ሰዎች ለሥራ አመች ሜዳ የማይፈቅዱ እንደነበሩ ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ በመንግሥት ውስጥ ያሉ መንግሥታት ማንሳት አስፈላጊ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙንና የደህንነት ሹሙን በአንድ ጊዜ ማንሳታቸውን ነው ያስታወሱት፡፡ የደህንነት ሹሙ ከስልጣን ሲነሱ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ሰርቀው ወደ መቀሌ መሄዳቸውንም ነው የተናሩት፡፡

<በኢትዮጵያ የመጀሪያው የጨረር ህክምና መሳሪያ ተመረቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!>

የተሰረቀው መሳሪያ የታወቀውም ከሰኔ 16 የግድያ ሙከራ በኃላ በተደረገ የተቋሙ ፍተሻ እንደሆነም አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ቢያንስ መሳሪያውን ይመለስ በሚል ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር መወያዬታቸውንም ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ ፈታኝ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመከላከያ ተቋሙን፣ የደህንነት ተቋማት፣ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት ተቋም፣ የፖሊስ፣ የገንዝብ ደኅንነት ተቋማትን መለወጥ እንዳስፈለገም አስታውሰዋል፡፡

በመከላከያ ተቋም ባለ አራት ኮከብ ጄኔራሎች ከትግራይ ክልል 60 በመቶ፣ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ 40 በመቶ ብቻ ነበሩ ነው ያሉት፡፡ ሌትናል ጄኔራል ደግሞ 50 በመቶ ከትግራይ ክልል የነበሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ሜጄር ጄኔራል 45 በመቶ፣ ብርጋዴል ጄነራል 40 በመቶ፣ ኮሎኔል 58 በመቶ፣ ሌትናል ኮሎኔል 66 በመቶ፣ ሺሕ አለቃ 53 በመቶ ከአንድ አካባቢ የመጡ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ በዚህ አካሄድ መከላከያውን ሚዛናዊ የሆነ ተቋም ለመፍጠር አስቸጋሪ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡

መከላከያውን አመራር የሚሰጠው ኃይል 80 በመቶው የሚሆነው ከትግራይ ክልል የመጣ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡ በሀገሪቱ የነበሩ እዞች ዋና አዛዥና ምክትል አዛዥ ሙሉ በሙሉ ከትግራይ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ከሰሜን እዝ ውጭ በሌሎቹ እዞች ሎጂስቲክና የሰው ኃይል ከሌሎች ክልሎች የተውጣጡ ነበሩበት፡፡ በሰሜን እዝ ግን አዛዥ፣ ምክትል አዛዥ፣ ሎጂስቲክስና ሰው ኃይል አስተዳደር አራቱም ከትግራይ የመጡ መሆናቸውን ነው ያስታወሱት፡፡

<አገር ማፍረስ ወንጀል በሕግ የሚፈለጉ 8 ግለሰበች>

የኢትዮጵያ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር መቶ በመቶ ከትግራይ ክልል የሆኑ እግረኛ ክፍለ ጦር ደግሞ 80 በመቶ ከትግራይ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡ ሜካናይዝድ ብርጌዶች 85 በመቶና እግረኛ ብርጌድ 80 በመቶ ከትግራይ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡የመካለከያ ተቋም ስልጠና ተቋማት 85 በመቶ በትግራይ ተወላጆች ሲመራ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ ይህን የተዛባ አካሄድ የትግራይ ህዝብ ሆነ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ እንዳለበትና መደገም እንደሌለበትም ነው ያስገነዘቡት፡፡

የሙያ ብቃት እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም በሚገባው መውሰድ እንደሚገባው ነው ያሳሰቡት፡፡ ኢትዮጵያን የሚመስል መከላከያ መገንባት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ካሁን ቀደም የተገነባበት ስርዓትም የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል ለመወሰን የሚያስቸግር እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የደህንነት እና የመከላከያ ተቋም ስሪት ለበርካታ ግጭቶች መነሻ እንደነበሩም ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለተከሰቱት ግጭቶች መነሻው ትግራይ ክልል ውስጥ የመሸጉት ቡድኖች እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡ እነዚህ የቡድን ስብስቦች የሀገር ውስጥ ብጥብጥ ከመፍጠር ባለፈ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለማጋጬት ብዙ ሙከራ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡ከለዉጡ በኃላ የመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ማሻሻያ እንደተደረገበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ወታደሩ የህዝብ እንጂ የብልጽግና እንዳይሆን መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe