የመከላከያ ሠራዊት ደርሶበት የነበረውን ጥቃት በማካካስ የህግ የበላይነትን የማስከበር ተግባሩን እየተወጣ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አስታወቀ

በሰሜን ዕዝ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ደርሶበት የነበረውን ጥቃት በማካካስ አሁን ላይ የህግ የበላይነትን የማስከበር ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን አዲስ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አስታውቋል፡፡
በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ በትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ደርሶበት የነበረው ጥቃትን ተከትሎ ሠራዊቱ ህግ ወደ ማስከበር ስራ መግባቱን ሴክሬታሪያቱ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳሉት የትግራይ ልዩ ኃይል ከአማራ ክልል ጋር ግጭት እንዲፈጥር የሚታዩ ትንኮሳዎች እየታዩ ነው፡፡ሠራዊቱ አሁንም ቢሆን የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየሰራ መሆኑን የገለፁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የትግራይ የመከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ህዝብ ጋር ዋጋ በከፈለ የጥቃት ዒላማ መሆኑ የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የትግራይ ክልልም ሆነ ኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ተገንዝቦ ከሠራዊቱ ጎን እንዲሰለፍ አሳስበዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት ኃላፊ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው የተፈጠረው ግጭት በአጠቃላይ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል ሳይሆን ከተወሰኑ ጥቅመኛ ስብስቦች ጋር የተፈጠረ ግጭት መሆኑን የክልሉ ህዝብ ሊረዳ ይግባል ብለዋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊቱ ደርሶበት የነበረውን ጥቃት በማካካስ አሁን ላይ የህግ የበላይነትን የማስከበር ተግባር እና ቦታዎችን የመቆጣጠር ሥራዎችን በመሥራት ላይ መሆኑንም አምባሳደር ሬድዋን ገልፀዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያቱም ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ ለህዝቡ እንደሚያደርስ አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe