የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የመኪና ሹፌር አማሟት በመኪና አደጋ ነበር

የመጨረሻው ቀልዳቸው እንዲህ ነበር
ነጋድራስ ተሰማን ለሞት ያበቃቸው አየር ሀይል የነበረ ልጃቸው በአውሮፕላን አደጋ መሞቱን ሰምተው እታች በምትታየው ጂፕ መኪናቸውን በድንጋጤ ሲነዱ መኪናዋ ተገልብጣ አንጎላቸው ላይ ደም በመፍሰሱ ሆስፒታል ገብተው ጥቂት ከተረዱ በኋላ ነው።
ነጋድራስ የገቡበት ሆስፒታል በዚያን ጊዜ ቀኃሥ በሚባለው ነበር። እሳቸው የልጅ እያሱ የቅርብ ወዳጅ ስለነበሩ ከቀኃሥ ጋር ጠበኛ ነበሩ።
እድል ቢገኙ ቁጥር ቅኔና አግብኦ በመጠቀም ቀኃሥን ጠቆም ጠቆም ስለሚያደርጓቸው እሳቸውም በተቻላቸው መጠን አያስጠጓቸውም ነበር።
ቀኃሥ በሳምንት አንድ ቀን ሆስፒታል እየሄዱ ህሙማን ይጠይቁና ያበረታቱ ነበር። ሆስፒታል ሲጎበኙ ሰው አንዱ በር ላይ ተሰብስቦ ሲያዩ ፤ ማነው እዚያ የተኛው ብለው ሲጠይቁ ፤ ተሰማ እሸቴ ናቸው ሲባሉ ካባቸውን ሲናደዱ ገፋ እንደሚያደርጉት አድርገው ፈጠን ፈጠን ማለት ሲጀምሩ ፤ አንድ ተከታይ ጠጋ ብለው ፤ ጃንሆይ ነጋድራስ እራሳቸው ውስጥ ደም ፈሶ መናገር ስለማይችሉ ምናለ ቢያዩዋቸው ብለው አሳሰቡ። ይሂን ሲሰሙ ንጉሥ ፤ እሺ መልካም ብለው ነጋድራስ ክፍል ገቡ። ሁለቱም ተያዩና ጃንሆይ እግዜር ይማርህ ፤ መጨረሻ ላይ ምላስህ ተያዘች አሏቸው ፤ መልስ አይሰጡኝም ብለው። ነጋድራስም ምላሳቸውን በደምብ አውጥተው እምም አሏቸው ይባላል።
ጃንሆይም አሁንም ያ አሽሙር እንዳልቀረና እንደ ተሸነፉ ሲያውቁ ካባቸውን ዘንጠፍ አድርገው በንዴት ወጡ ይባላል።
ነጋድራስ የሞቱት ጥቅምት 3 1957 በ87 አመታቸው ነበር። ታላቅ ቀብር ነበር። እኔም አይቸዋለሁ።
ነጋድራስ ተሰማ የመጀመሪያው ሹፌር ብቻ ሳይሆኑ ፤ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ድምጽ በዲስክ በጀርመን አገር አስቀጂ ፤ በጀርመን አገር አርት ተማሪና የመጀመሪያው ዘመናዊ ያገራችን ሀውልት ሰሪ ፤ ያማሪኛ ሊቅ ወዘተ ነበሩ።
ነጋድራስ ስምንት ቋንቋ ይችሉ ነበር ፠ አማርኛ ፤ አፋን ኦሮሞ ፤ አደርኛ ፤ አረብኛ ፤ ፈረንሳይኛ ፤ ጣልያንኛ ፤ ጀርመንኛ።
ባገራችን መሬት ስንት ዋርካ ነበረን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር💚💛❤️

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe