የሚዲያና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ያቀፈ አስቸኳይ ግብረ ሃይል እንቋቋም ተጠየቀ

 የከተማ አስተዳደሩ ጥያቄውን ተቀብሎታል፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ሰሞኑን ለአርቲስቶችና ለሚዲያ ባለሙያዎች በዝግ ባዘጋጀው መድረክ ላይ የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተገኙ ሲሆን መንግስት እያገኘ ስላላው የጦር ሜዳ ድልና ቀጣይ አቅጣጫ ውይይት ተካሂዷል፡፡

መንግሥት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት የሚጠቁም የውይይት መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት ከከተማ አስተዳደሩ የተወከሉት አቶ ቢንያም ምክሩ፣የተባሉ ግለሰብ  ቀጣይ የመንገስትን  ሥራዎች ያብራሩ ሲሆን አርቲስቶና የሚዲያ ባለሙያዎች በበኩላቸው አሉ ያሏቸውን ችግሮችና የመፍትሔ ሀሳቦችን ገልፀዋል፡፡

በጋዜጠኞችና በሚዲያ አመራሮች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል አገርን የሚጠቅም ሥራ ለመሥራት፣ የሚዲያው ምኅዳር ጠቧል የሚለው ጥያቄ ቀዳሚ ነበር፡፡ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ተንቀሳቅሶ ለመሥራት ብዙ ችግር አለ ብለዋል ተሳታፊዎቹ፤

የኪነ ጥበብ ባለሙያው ችግር ሲፈጠርና አደጋ ሲኖር ብቻ ለአገራዊ ጉዳይ የሚጠራ ብቻ ሳይሆን፣ ወጥነት ባለው መንገድ በአገር ጉዳይ መሳተፍ እንደሚኖርበት ተገልጿል፡፡ የኪነ ጥበብ ፈንድ ይቋቋምልን፣ በመላው አገሪቱ በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ መሆን የሚችል የጥበብ ሥራ ለማበርከት ምቹ ሁኔታ ይፈጠርልን ሲሉም፣ ከያኒያኑ የዘርፋቸውን ተግዳሮቶች አንድ በአንድ ዘርዝርዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በበኩላቸው በኢትዮጵያ የገባችበት ጦርነት የእጅ አዙር ጦርነት ውጤት መሆኑን አመልክተው በዚህ ጦርነት የተነሳ የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ አገሪቱ ለከፋ አደጋ እንዳትዳረግ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ሊረባብ  ይገባል ብለዋል፤

በእነዚህና በሌሎች ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ሐሳቦች የተስተጋባበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስብሰባ፣ የኪነ ጥበብና የሚዲያ ሰዎችን ያቀፈ አንድ ማኅበር ይመሥረት የሚለውን ጥያቄ የተንፀባረቀበት ሲሆን  ከሙያተኞቹ የቀረበውን ይህን ጥያቄ በትኩረት የተቀበለው የከተማ አስተዳደሩ  ከሁለቱም ሙያዎች በአስቸኳይ አንድ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ፣ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ ቃል ገብቷል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe