የሞባይል ሲም ካርድ ማቀፊያዎችን በህፃናት የንፅህና መጠበቂያ ( ዳይፐር) በመደበቅ ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት የሞከሩ በወንጀል ተቀጡ

የሞባይል ሲም ካርድ ማቀፊያዎችን በህፃናት የንፅህና መጠበቂያ ( ዳይፐር) ውስጥ በመደበቅ ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት ሲሞከሩ የተያዙት ተከሳሾች በፈፀሙት የኮንትሮባንድ ወንጀል በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ተወሰነባቸው ።
ከዱባይ ከተማ ወደ ሃገር ውስጥ የሞባይል ሲም ካርድ ማቀፊያዎችን በህፃናት የንፅህና መጠበቂያ ( ዳይፐር) ውስጥ በመደበቅ ለማስገባት ሲሞከሩ የተያዙት ተከሳሾች በፈፀሙት የኮንትሮባንድ ወንጀል በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል ።
የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው
ግሩም ጌታሁንና ሀፌዛ ይድንቃቸው የተባሉት ተከሳሾች የጉምርክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 168 (1) በአዋጅ ቁጥር 1160/2011 እንደተሸሻለው አንቀፅ 44 ላይ የተመለከተውን በተላለፍቸው ነው በዐቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸው ።
ተከሳሾቹ ጳጉሜ 02/2012 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ሲሆን ከዱባይ ከተማ ተነስተው ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የገቢ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ሲደርሱ በተደረገላቸው የኤክስሬይ እና ዝርዝር የዕቃ ፍተሻ ሲደርግባቸው የጉምሩክ ስነ ስርዓት ያልተፈፀመባቸው የቀረጥና ታክስ መጠናቸው 75.464.27 ( ሰባ አምስት ሺህ አራት መቶ ስልሳ አራት ብር ከሃያ ሰባት ሳንቲም) የሚያወጡ ግሩም ጌታሁን 2‚430 ሀፊዛ ይድነቃቸው ደግሞ 2‚500 የሞባይ ሲም ካርድ ማቀፊያዎችን በዕለቱ በያዟቸው ሻንጣዎች ውስጥ በፕላስተር አሽገው በህፃናት የንፅህና መጠበቂያ (ዳይፐር ) ውስጥ በመደበቅ ወደ ሀገር ሊያስገቡ ሲሉ የተያዙ በመሆኑ በፈፀሙት የኮንትሮባንድ ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተምሰርቶባቸዋል ።
ተከሳሾች በችሎት ቀርበው እምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ ድርጊቱን አልፈፀምንም ጥፋተኛም አይደለንም ምክንያቱም ከዚህ በፊት ይዘን መጥተን ስለምናውቅ ወንጀል መሆኑን አናውቅም በማለት ክደው የተከራከሩ በመሆኑ ዓቃቤ ህግም የሰው፣ የሰነድ፣ ገላጭ እና የኤግዚቢት ማሰረጃዎችን በማቅረብ አስረድቷል፡፡
ሆኖም ተከሳሾች በዐቃቤ ህግ ማስረጃ የቀረበባቸውን ክስ በመከላከያ ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላችው ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል፡፡
በዚህም መሰረት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ4 ዓመት ፅኑ እስራትና በ35 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል ።(ፍትሕ ሚኒስቴር)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe