የሪህ ሕመምን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚረዱ የጤና ምክሮች!

የሪህ ሕመምን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚረዱ የጤና ምክሮች! | Health Tips for Managing Gouty Arthritis!
ሪህ ምንድን ነው? | What is Gouty Arthritis?
ሪህ በደም ውስጥ ያለው የ ዩሪክ አሲድ (Uric acid) መጠን ከመጠን በላይ ሲጨምር የሚከሰት የመገጣጠሚያ ህመም አይነት ነው።
ይህ አሲድ በመገጣጠሚያዎች ውስጥ እንደ መርፌ የሚወጉ ትናንሽ ክሪስታሎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል።
ይህም ድንገተኛና ከፍተኛ የሆነ ህመም ያስከትላል፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በትልቁ የእግር ጣት ላይ ይጀምራል።
ሊተገብሯቸው የሚገቡ ቁልፍ ጠቃሚ ምክሮች! | Key Health Tips to Control Gout!
. በቂ ውሃ ይጠጡ! | Stay Hydrated!
ውሃ መጠጣት በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ትርፍ ዩሪክ አሲድ በሽንት መልክ ተወግዶ እንዲወጣ ይረዳል። በቀን ቢያንስ ከ8-10 ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ።
. ከፍተኛ የ”ፑሪን” (ˈpyo͝oˌrēn) መጠን ያላቸውን ምግቦች ይቀንሱ! | Limit High-Purine Foods!
ፑሪን የተባለው ንጥረ-ነገር በሰውነታችን ውስጥ ወደ ዩሪክ አሲድነት ይቀየራል። ስለዚህ የሚከተሉትን ምግቦች መቀነስ ተገቢ ነው፦
ቀይ ስጋ እና እንደ ጉበት፣ እና ኩላሊት ያሉ የውስጥ እቃዎች።
አንዳንድ የባህር ምግቦች (እንደ ሰርዲን ያሉ)።
በፋብሪካ የተቀነባበሩና ቅባት የበዛባቸው ምግቦች።
. ስኳርና ጣፋጭ ነገሮችን ይቀንሱ! | Cut Down on Sugary Foods & Drinks!
ለስላሳ መጠጦች፣ ሰው ሰራሽ ስኳር በብዛት የተጨመረባቸው መጠጦች፣ እና ምግቦች በደም ውስጥ ያለውን የዩሪክ አሲድ መጠን ከፍ ያደርጋሉ።
. ከአልኮል መጠጥ ይቆጠቡ! | Avoid Excess Alcohol!
የአልኮል መጠጦች (በተለይም ቢራ) ሰውነታችን ዩሪክ አሲድን የማስወገድ ብቃቱን እንዲቀንስ በማድረግ ለሪህ ህመም መቀስቀስ ትልቅ ምክንያት ይሆናል።
. ጤናማ የሰውነት ክብደት ይኑርዎት! | Maintain a Healthy Weight!
ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት ለዩሪክ አሲድ መመረት ምክንያት ይሆናል።
ነገር ግን ክብደት ለመቀነስ ሲባል ምግብን ሙሉ በሙሉ መተው/ማቆም (Crash dieting) ራሱ ህመሙን ሊያባብሰው ስለሚችል ቀስ በቀስ በጤናማ መንገድ ክብደትን መቀነስ ይመከራል።
. ለሪህ ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን ያዘውትሩ! | Eat Gout-Friendly Foods!
አትክልቶችና ፍራፍሬዎች፦ (በተለይ ቼሪ (Cherries) የሪህ ህመምን ለመቀነስ እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ)።
ጥራጥሬዎችና እህሎች።
ቅባታቸው የቀነሰ የወተት ተዋጽኦዎች።
. መደበኛ እንቅስቃሴ ያድርጉ! | Exercise Regularly!
ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የመገጣጠሚያዎችን ጤንነት ለመጠበቅና የሰውነት ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል።
. መድሃኒትን በአግባቡ ይውሰዱ! | Take Medications as Prescribed!
ሐኪምዎ ያዘዘልዎትን የህመም ማስታገሻም ሆነ የዩሪክ አሲድ መጠንን የሚቀንሱ መድሃኒቶችን (እንደ Colchicine ያሉ) በትክክል ይውሰዱ።
. ተጓዳኝ የጤና እክሎችን ይቆጣጠሩ! |Manage Other Health Conditions!
እንደ ደም ግፊት፣ የኩላሊት በሽታ፣ እና ስኳር ያሉ ተጓዳኝ ህመሞች ካሉብዎት፤ እነሱን በአግባቡ መቆጣጠር የሪህ ህመምን ለመቀነስ ይረዳል።
. የህመም ምልክቶችን ቀድመው ይለዩ! | Recognize Early Symptoms!
የመገጣጠሚያ ህመም፣ መቅላት፣ ወይም እብጠት ሲያዩ ወይም ሲጀምርዎት ወዲያውኑ ህክምና መጀመር ህመሙ እንዳይጠነክርና/እንዳይበረታ እና ረጅም ጊዜ እንዳይቆይ ያደርጋል።
ሐኪም ማማከር የሚገባዎት መቼ ነው? | When to See a Doctor?
ድንገተኛና ሊታገሱት የማይችሉት ከፍተኛ የመገጣጠሚያ ህመም ሲኖር (በተለይ በሌሊት)።
የሪህ ህመሙ በተደጋጋሚ የሚመላለስብዎ ከሆነ።
ከህመሙ ጋር የኢንፌክሽን ምልክቶች (ትኩሳት፣ ከፍተኛ እብጠት) ካዩ/ካሉ።
ማጠቃለያ! | Final Insight!
ሪህ በአመጋገብና በአኗኗር ዘይቤ ለውጥ እንዲሁም በህክምና በቀላሉ ሊቆጣጠሩት የሚችሉት ህመም/በሽታ ነው።
ውሃ አዘውትሮ መጠጣት፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ እንዲሁም ቋሚ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ የህመሙን መቀስቀስ ወይም (ከህመሙ ነጻ ለመሆን) እና በመገጣጠሚያዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ዘላቂ ጉዳት ለመከላከል ወሳኝ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe