” የራስ መንገድን ” ፊልም በሁለት ቢሊዮን ብር ለሚገነባው ግዙፍ የኩላሊት መታከሚያ ሆስፒታል ማስጀመሪያ ይውላል::

 ” የራስ መንገድን ” ፊልም ትኬት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በቻለው አቅም ሁሉ በመግዛት እንዲሳተፍ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ጥሪውን አስተላልፏል።
ድርሰትና ዝግጅቱ የአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ የሆነው “የራስ መንገድ” ፊልም የፊታችን ሰኞ ነሐሴ 16 ቀን 2014 በስካይ ላይት ሆቴል ያስመርቃል።ይህንኑ ለበጎ አላማ የሚውለውን የፊልም ምርቃት ፕሮግራም አስመልክቶ ዛሬ በብሔራዊ ቲያትር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ተስጥቷል:: ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጡት አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ አርቲስት ሳምሶን ቤቢ :ሳሙሄል መልካሙ ከቦርኮታ ፊልም ፕሮዳክሽን እንዲህም ሀብታሙ ደጀኔ አሜዚንግ ፕሮሞሽን በጋራ በመሆን ነው::
አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው በአቅማቸው የሚታከሙበትን ቋሚ የሆነ የኩላሊት ታማሚዎች የሚታከሙበትን ሆስፒታል ለመገንባት በህብረት ለበጎ ድርጅትና ከጏደኞቹ ጋር በመሆን በለገጣፎ 60,000 ካሬ ቦታ ተረክቧል:: በህብረት ለበጎ እና አማካኝነት እና ከቅርብ ጓደኞቹ እና ወዳጆቹ ጋር በመሆን የመሬቱን ለሆስፒታል ግንባታ የተረከበውን የመሬት ካሳ ክፍያ ተከፍሎ እንደተጠናቀቀ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል::
ሆስፒታል ለመገንባት ሁለት ቢልየን ብር እንደሚፈጅ የትገለፀ ሲሆን ይህንን ሆስፒታል ግንባታ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል::
በመሆኑም ለዚህ ሆስፒታል ግንባታ ከሚያግዙት የገቢ ማስገኛ ከ14 ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ተደርሶ የተዘጋጀውና በርካታ አንጋፋና ተወዳጅ ተዋንያን የተሳተፉበትን “የራስ መንገድ” ፊልምን በልዩ ፕሮግራም የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 16/2014 ዓ/ም በስካይ ላይት ሆቴል በመግቢያ ዋጋ እራትን ጨምሮ መግቢያው 2 ሺ ብር ሲሆን ከቀኑ 10:30 ጀምሮ ለምረቃ ይበቃል።
በእዚህ የምረቃ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሀገራችን ታዋቂ አርቲስቶች የሚገኙ ይሆናል። ይህም ሆስፒታሉን ለመገንባት በህብረት ለበጎ ድርጅት ከተያዙ 14 ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ አንዱ መሆኑን አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል:: በመሆኑም ኢትዮጵያውያን በቻለው አቅም ሁሉ እንዲሳተፍ ጥሪውን አስተላልፏል።
የፊልሙ ምርቃት በ ኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዢን በቀጥታ ይተላለፋል።
የመግቢያ ዋጋ እራትን ጨምሮ 2000 (ሁለት ሺህ) ብር ነው::
የፊልሙን የመግቢያ ትኬቱን በአሜዚንግ ማስታወቂያና ኢቨንት ቢሮ ያገኙታል
ስልክ :-
+251 9 80 11 36 34
+251 9 11 65 48 00
(ይትባረክ ዋለልኝ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe