የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ለተቀዛቀዘው የጅቡቲ ኢኮኖሚ መሻሻል አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት/ IMF አስታወቀ

ከሳምንታት በፊት የ IMF ልኡካን በድርጅቱ በአንቀጽ 4 መሰረት በጅቡቲ ተገኝቶ ውይይቶች አድርጎ ባወጣው መግለጫ እንደገልፀው በኢትዮጵያ የሰሜን ግጭት የጅቡቲ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጫና አሳርፎ ነበር፡፡

በተለይ ከኢትዮጵያው የውስጥ ግጭት ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምህዋር የሆነው የወደብ እንቅስቃሴ መቀነሱን አስታውሷል፡፡

በተጨማሪም የሸቀጥ ዋጋ መናር እና ቀጠናዊ የድርቅ ሁኔታ ለዜጎች የመግዛት አቅም ተግዳሮት ነበር ያለው ድርጅቱ ይህም የመንግስትን ገቢ እንደቀነሰው ተናግሯል፡፡

በዚህም እኤአ በ2022 የጅቡቲ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ 2.5 በመቶ እንደሚሆን IMF በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

ባሳለፍነው ጥቅም በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራዩ አማጺ ቡድን የተደረሰው የሰላም ስምምነት ለጅቡቲ ኢኮኖሚ መልካም እንደሆነ የተናገረው IMF፤ ስምምነቱ ንግድ እንዲያገግም፣ የወደብ እንቅስቃሴ ወደ ቀድሞ ቦታው እንዲመለስ እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንት ከመሳብ አንጻር ሁነኛ ውጤት ሊኖረው እንደሚችል አስምሮበታል፡፡

በዚህም እኤአ በ2023 ጅቡቲ የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚኖራት ድርጅቱ ግምት ሰጥቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe