የሱዳን መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው በሜ/ጄ አብደል ባቂ በክራዊ የተመራ እንደነበር ገለፀ

በሜጀር ጄነራል አብደል ባቂ በክራዊ የሚመሩትና የግልበጣ ሙከራው አካል የሆኑ ወታደሮች በምስራቃዊ ሱዳን የሚገኘውን የሃገሪቱን ጦር ተቆጣጥረው እንደበር ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ወታደሮቹ ድልድዮችን እና የመተላለፊያ መንገዶችን ይዘው እንደነበር የተገለጸም ሲሆን የሃገሪቱን ብሔራዊ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያን ለመቆጣጠር በሙከራ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

ጣቢያው መደበኛ ስርጭቱን አቋርጦ የተለያዩ ሃገራዊ ይዘት ያላቸውን ሙዚቃዎች ይለቅም ነበር ተብሏል፡፡

ኦምዱርማንን ከሃገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም የሚያገናኘው ድልድይም በአሁኑ ወቅትም ተዘግቶ ይገኛል፡፡

ሆኖም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው በቁጥጥር ስር መዋሉን የሚያመለክቱ መረጃዎችም እየወጡ ነው፡፡የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ቃል አቀባይ “ነገሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ አብዮቱም ባለድል” ሆኗል ብለዋል፡፡

ሆኖም ሙከራው አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን እና በወታደሮቹ ይዞታ ስር የሚገኙ ነገሮችም እንዳሉ የሚያመለክቱ ዘገባዎች እየወጡ ነው።ከሰሞኑ በምስራቃዊ ሃገሪቱ አካባቢዎች አመጽ ተቀስቅሶ ነበር፡፡ አመጹ በቤጃ ጎሳ አባላት የተቀሰቀሰ ነበር፡፡

የጎሳ አባላቱ በምስራቅ ሱዳን ያሉ ወደቦችን ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ጋር የሚያገኘውን መንገድ ጭምር ዘግተው ነበር፡፡ለተቃውሞ መነሻ የሆነው የቤጃ ጎሳ አባላት የሚኖሩበት ግዛት ኋላ ቀር ነው የሚል መሆኑን የተለያዩ ሚዲያዎች እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡

የቤጃ ጠቅላይ ም/ቤት ተብሎ የሚጠራው የቤጃ ጎሳ አባላት ተቆርቋሪ ያሰማውን ጥሪ ተከትሎ ዋናው መንገድ 5 ቦታዎች በላይ መዘጋቱ ተዘግቧል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe