የሱዳን የፖለቲካ ቀውስ ኢጋድን አሳሰበው

የሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አስታወቀ፡፡

የኢጋድ ሥራ አስፈጻሚ በወቅታዊ የሱዳን ሁኔታ ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ሊቀመንበሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ መሆነን ገልጸዋል።

የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር እና የድርጅቱ መሥራች አባል በሆነችው ሱዳን የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ መፍትሔ እንዲያገኝ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የኢጋድ ሥራ አስፈፃሚ የሱዳን ሽግግር መንግሥትን ለማዳከም የሚደረገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ አጥብቆ የሚያወገዝ መሆኑን ገልጿል።

ኢጋድ የሱዳንን የሽግግር መንግሥት ለመደገፍ፣ የሕዝብ ሰላምን እና ዴሞክራሲን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኑን ዶ/ር ወርቅነህ አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe